በኦሮሚያ እና አማራ ክልሎች ሩዝን በስፋት ለማምረት ዝግጅት እየተደረገ እንደሚገኝ ተገልጿል፡፡
የኦሮሚያ ክልል ግብርና ቢሮ ምክትል ኃላፊ በሪሶ ፈይሳ፤በ2017/18 መኸር እርሻ 1 ነጥብ 5 ሚሊየን ሄክታር መሬት በሩዝ ሰብል ይሸፈናል ያሉ ሲሆን በመኸር ወቅት በሩዝ ሰብል የሚሸፈነው መሬት መለየቱን ገልጸው፤ከዚህም ከ40 ሚሊየን ኩንታል በላይ ምርት ይጠበቃል ብለዋል።
በተመሳሳይ በአማራ ክልል ከ400 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት በሩዝ ሰብል ለማልማት የማሳ ዝግጅት መደረጉን የክልሉ ግብርና ቢሮ የሰብል ልማትና ጥበቃ ዳይሬክተር ማንደፍሮ አስላከ (ዶ/ር) ገልጸዋል።
በዚህም በሄክታር 55 ኩንታል ምርት ለማግኘት እየተሰራ መሆኑን አመልክተዋል።
ፋሚኮ
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
ምላሽ ይስጡ