አንድን ምርት የተመረተበት አካባቢ በሚሰጠው ጥራት ወይም ልዩ ባህሪ መሰረት አድርጎ ለሸማቾች እንደሚያቀርቡ ይታወቃል፡፡ በዘመናዊው የንግድ ስርዓት ውስጥም የተለያዩ ምርቶች እና ቁሳቁሶች የሚመረቱበትን አካባቢ በመጠቀም ተወዳዳሪ ለማድረግ የመልከዓ ምድር አመላካች ረቂቅ የህግ ሰነድ ማዘጋጀቱን የኢትዮጵያ አእምሯዊ ንብረት ባለስልጣን አስታውቋል፡፡
የዓለም አእምሯዊ ንብረት ድርጅት ዳይሬክተር ጀነራል የተገኙበት አለምአቀፍ የመልክዓ ምድራዊ አመላካች ምርቶች ጥበቃ ኮንፈረንስ ተካሂዷል፡፡ ኢትዮጵያ በአእምሯዊ ንብረት ጥበቃ የጀመረችውን የለውጥ ስራዎች ለማበረታታት እና በዓለም አቀፉ የአእምሯዊ ንብረት ስርዓት ያላትን ተሳትፎ ለማሳደግ በተለይም በዘርፉ ከሌሎች ዓለም አቀፍ፣ አህጉራዊና አቻ ብሄራዊ ተቋማት ጋር ትብብሮችን ለማሳደግና ልዩ ልዩ ድጋፎች ያስፈልጋል ሲሉ የገለፁት የኢትዮጵያ የአእምሯዊ ንብረት ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ ወልዱ ይመሰል ናቸው።
በኮንፈረንሱ የተለያዩ ሃገራት የመልክዓ ምድራዊ አመላካች ምርቶች ጥበቃ ስርዓት ተሞክሮዎች የቀረቡ ሲሆን፤ በመገኛ ምንጫቸው ተለይተው የሚታወቁ ጥራታቸውና የገበያ ተፈላጊነታቸው ከሚመረቱበት አካባቢ ጋር በጥብቅ የተቆራኘ የግብርና ምርቶችን፤ የእደ ጥበብ ውጤቶችን እና ሌሎችን በመልክዓ ምድራዊ አመላካች ምርቶች ጥበቃ ስርዓት መምራት በምርትና አቅርቦት ሂደት ሰንሰለት ውስጥ ያሉ ተዋናዮችን በይበልጥ ተጠቃሚ እንደሚያደርግና በዓለም አቀፍ ገበያም ምርቶቹ ያላቸውን ዝና በአግባቡ ለመሸጥ ይጠቅማልም ብለዋል፡፡
ለዚህም ኢትዮጵያ በመገኛ ቦታቸው ተለይተው የሚታወቁና ዝናና ጥራት ያላቸውን ምርቶች በመልክዓ ምድራዊ አመላካች ሥርዓት በዓለም አቀፍ ገበያ ተፈላጊ ለማድረግ የህግ ማዕቀፍ መዘጋጀቱ በመድረኩ ተገልጿል ።
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
ምላሽ ይስጡ