ፓርቲዎች ከቀጣይ አመት መጀመሪያ ወራት ጀምሮ ፖሊሲያቸውን ለህዝብና ለመገናኛ ብዙሃን ማቅረብ እንደሚጀምሩ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ዛሬ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ አስታውቋል።
ቦርዱ 7ተኛው ጠቅላላ አገራዊ ምርጫ ባተሻለ መልኩ ማስፈፀም የሚያስችለውን አዋጅ ለምክር ቤት እንደላከ ያስታወቁት የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ ዋና ሰብሳቢ ወ/ሮ ሜላተወርቅ ኃይሉ፤ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በአዲሱ አዋጅ ዙሪያ የተደረገውን ወይይት ተከትሎ የተገኙ ግብዓቶች መካተታቸውን ተናግረዋል።
ቀጣይ አመት ይደረጋል ተብሎ በሚጠበቀው ምርጫ በዘመናዊ መልኩ በቴክኖሎጂ በመታገዝ የመራጮች ምዝገባ እንደሚከናውን በመግለጽ፤ ፓርቲዎችም አባላቶቻቸውን በቴክኖሎጂ በመታገዝ እንዲመዘግቡ የሚያስችል ሶፍትዌር መበልጸጉን ተናግረዋል።
ቦርዱ በተመሳሳይ እጩዎችንም መመዝገብ የሚያስችለውን ሶፍትዌር ማበልፀጉን ነው ያስታወቀው።
በ7ተኛው ጠቅላላ አገራዊ ምርጫ ቴክኖሎጂን በስፋት ስራ ላይ ለማዋል ቦርዱ በርካታ ስራዎችን እየሰራ መሆኑን ዋና ሰብሳቢዋ አመላክተዋል።
ምላሽ ይስጡ