በጤና ሚኒስቴር በኩል የቅድመ ዝግጅት እና የቅኝት ስራዎች እየተሰሩ ቢሆንም በኢትዮጵያ በዝንጀሮ ፈንጣጣ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር ሊጨምር እንደሚችል ሚኒስቴሩ ለመናኸሪያ ሬድዮ አስታውቋል፡፡
በኢትዮጵያ ባለፉት ቀናት 15 የላብራቶሪ ምርመራ ተካሂዶ 6 ሰዎች በበሽታው መያዛቸው መረጋገጡን እና የ1 ሰው ህይወት ማለፉን የሚናገሩት በጤና ሚኒስቴር የህክምና አገልግሎት መሪ ስራ አስፈፃሚ ዶክተር ኢሊባቡር ቦኖ ናቸው፡፡
የዝንጀሮ ፈንጣጣ ልክ እንደ ኮሮና ወረርሽኝ በቀላሉ የመተላለፍ እድል ያለው በመሆኑ በሃገራችን የመሰራጨት ዕድሉ ከፍተኛ ነው ሲሉ ገልጸዋል፡፡
ማህበረሰቡ ከጤና ሚኒስቴር እና ከባለድርሻ አካላት የሚወጡ መረጃዎችን በመከታተል ራሱን እንዲጠብቅ እና ስርጭቱን መቀነስ እንደሚገባ ዶክተር ኢሊባቡር አሳስበዋል፡፡
ህብረተሰቡ ማንኛውንም አይነት ምልክቶች ሲያስተውልና ሲጠራጠር ለጤና ተቋማት እንዲያሳዉቅ የጠየቁት መሪ ስራ አስፈፃሚው፤ ድንገተኛ የወረርሽኝ አደጋዎችን ለመከላከልና ለመቆጣጠር ሚኒስቴሩ ከኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ጋር በትብብር እየሰራ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
ምላሽ ይስጡ