የኢትዮጵያ ደረጃዎች ኢንስቲትዩት ከባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን በ5 ዘርፎች ተዘጋጅተው ከቀረቡለት 63 አስገዳጅ እና ሌሎችም የኢትዮጵያ ደረጃዎች 34ቱን ማፅደቁን የኢንስቲትዩቱ ደረጃ ዝግጅት ስራ አስፈፃሚ አቶ ይልማ መንግስቱ አስታውቀዋል።
19ኙ ደረጃዎች አዳዲስ ሲሆኑ፤ 15ቱ ደግሞ የተከለሱ ረቂቅ የኢትዮጵያ ደረጃዎች መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡
ከነዚህም መካከል 10ሩ አዲስ ደረጃዎች በአከባቢ ጤናና ደህንነት ዘርፍ ላይ ትኩረት ያደረጉ ሲሆን፣ የተከለሱ የህክምና እና የጤና መጠበቂያ መሳሪያዎችን የተመለከቱትን ጨምሮ በጠቅላላው 19 ጤናን የሚመለከቱ ደረጃዎች መጽደቃቸውን ተናግረዋል፡፡
በግብርና እና ምግብ ዘርፍ 9 አዳዲስ እና 6 የተከለሱ በጠቅላላው 15 ደረጃዎች መጽደቃቸውም ተገልጻል::ከጸደቁ ደረጃዎች መካከል 18ቱ አስገዳጅ መሆናቸውንም ኢንስቲትዩቱ አስታውቋል።
የጸደቁት ደረጃዎች ለአካባቢ ጥበቃ እና የሸማቾችን ጥቅም ከማስጠበቅ አንጻር አዎንታዊ ፋይዳ እንዳላቸው ነው የተመላከተው፡፡
በመሆኑም አምራቾች እና ሸማቾች የደረጃዎቹን መኖር አውቀው ደረጃዎቹን በመጠቀም የምርቶቻቸውን ጥራት በማሻሻል ተወዳዳሪ ምርቶችን ለውጭ ገበያ በመላክ ለሀገር ኢኮኖሚ አስተዋጽኦ እንዲያደርጉ ጥሪ ቀርቧል።
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
ምላሽ ይስጡ