በኢትዮጵያ በአሁ ወቅት አገልግሎት የሚሰጡ በርካታ የተሃድሶ ማዕከላት ቢኖሩም በቂ አለመሆናቸውን የጤና ሚኒስቴር አስታወቋል።
በአሁኑ ወቅት ከ22 በላይ የተሃድሶ ማዕከላት ቢሮም በቂ አለመሆናቸውን እና ፈጣን ትኩረት የሚሹ ወሳኝ ችግሮች እንዳሉ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ገልጿል።
በሃገር ውስጥ የሚመረቱ የአጋዝ ቴክኖሎጂ መሳሪያዎች አቅርቦት ውስንነት ከውጭ የሚገቡ የአጋዝ ቴክኖሎጂዎች የብዙዎችን የመግዛት አቅም ያላገናዘበ መሆኑ፤ አገልግሎት ሰጪ ባለሙያዎች በቂ ግንዛቤ እና የስልጠና ክፍቶች መኖራቸውን ሚኒስቴር መስሪያቤቱ አስታውቋል።
የአጋዥ ቴክኖሎጂ መሳሪያዎችና አገልግሎቶች አቅርቦት ላይ ከፍተኛ ክፍተት መኖሩ በተለይ በገጠርና ራቅ ባሉ ቦታዎች አገልግሎት ማግኘት ፈታኝ ሁኖ መቆየቱ ችግሩን ዘላቂ እንዳደረገው ተገልጿል።
በኢትዮጵያ ውስጥ ህፃናትና አረጋውያን ሴቶች እና አካል ጉዳተኞችን ጨምሮ በሚሊዮን የሚቆጠሩ የማህበረሰብ ክፍሎች በህብረተሰቡ ውስጥ ሙሉበሙሉ ተሳትፎ እንዳይኖቸው የሚከለክሉ አሰረሮች መኖራቸዉ ተገልጿል፡፡
በመሆኑም ከአጋር አካላት ጋር በመስራት የፖሊሲ ማዕቀፎችን በማጠናከር እና በአገር ውስጥ ምርት ላይ ኢንቨስት በማድረግ አጋዥ ቴክኖሎጂ ለሁሉም ኢትዮጵያን በተመጣጣኝ ዋጋ ተደራሽ ለማድረግ እየሰራ እንደሆነም ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ አመላክቷል።
ሁለተኛው ሀገር አቀፍ ዓመታዊ የአጋዥ ቴክኖሎጂ ኮንፈረንስን ”በአጋዥ ቴክኖሎጂ አለመቻልን እንግታ” በልየታ/ በምርትና አቅርቦት / በአካታችነት በሚል መሪ ቃል በቤኒሻጉል ጉምዝ ክልል በአሶሳ ከተማ እየተከበረ ይገኛል።
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
ምላሽ ይስጡ