ግንቦት 20 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ)የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር በወላጆቻቸው ጥፋት ምክንያት አብረዋቸው ማረሚያ ለሚገቡት ህፃናት የሚደረገውን ድጋፍ ለማሻሻል እየተሰራ ነው ብሏል፡፡
የክስ ማቅለያ ይደረግልናል በሚል በሃሰተኛ ምስክር ሁለትና ከዛ በላይ ልጆቻቸውን ይዘው ማረመያ የሚገቡ ወላጆች መበራከት ለህፃናቱ ልዩ ክትትል ለማድረግ በሚሰራው ስራ ላይ ተግዳሮት እየፈጠረ መሆኑን ሚኒስቴሩ ገልጿል፡፡
ይህንን በተመለከተ ለብቻው የተቀመጠ መብትና ድንጋጌ አለመኖሩ ለስራው ተግዳሮት እንደፈጠረበት ለጣቢያችን ገልጿል::
ለህፃናቱ ለብቻ የተመደበላቸው በጀት ካለመኖሩም በተጨማሪ የህግ ክፍተትም እንዳለ የተናገሩት በሚንስቴሩ የህፃናት መብት ጥበቃ መሪ ስራ አስፈፃሚ ዘቢደር ቦጋለ፤ አሰራሩን ለማሻሻል እየተሰራ ነው ብለዋል።
የህፃናቱን የመብት ድንጋጌን ተከትሎ መፍትሔ እንዲያገኝ ከባለድርሻ አካላት ጋር እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል።
ህፃናቱ ተገቢውን ትኩረት እንዲያገኙ ለሚመለከታቸው አካላት ሰፊ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራ እየተሰራ መሆኑንና መብታቸውን በማስጠበቁ ረገድ የቁጥጥር ስራዎችም እየተሰሩ እንዳሉ መሪ ስራ አስፈጻሚው ገልጸዋል፡፡
ይሁን እንጅ በቁጥጥር ሂደቱ እስካሁን ተጠያቂ የተደረገ ማረሚያ ቤት እንደሌለ ነው ያስታወቁት።
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
ምላሽ ይስጡ