የኢትዮጵያ እሳተ ገሞራዎች ውስጥ እጅግ ብርቅዬ የሚባለውን ሰማያዊ ላቫ እየፈነጠቀ መሆኑ እንደ ክስተት እየታየ ይገኛል። ከኢንዶኔዢያ ጃቫ ግዛት ካዋ ኢጄን እሳተ ገሞራ ጋር ተመሳሳይነት አለው የተባለው ሰማያዊ ላቫው በመጀመሪያ እይታ ላቫው ከተራራው ላይ እየፈሰሰ ይመስላል፣ ነገር ግን ይህ ያልተለመደ ፍካት እንደሚታሰበው አይደለም።
“ሰማያዊ እሳት” እየተባለ የሚጠራው ይህ ክስተት በላቫ የተፈጠረ ሳይሆን ከእሳተ ገሞራው ስንጥቆች በሚወጡት የሚቃጠሉ የሰልፈር ጋዞች የሚመጣ መሆኑ ተገልጿል። እስከ 600°C (1,100°F) የሚደርስ ሙቀት ያላቸው ትኩስ ጋዞች በአየር ውስጥ ከሚገኘው ኦክሲጅን ጋር ሲገናኙ፣ በእሳት ተያይዘው ደማቅ ሰማያዊ ነበልባል ይፈጥራሉ።
በካዋህ ኢጄን ያለው ትክክለኛው ላቫ እንደ አብዛኞቹ እሳተ ገሞራዎች የተለመደው ቀይ-ብርቱካናማ ቀለም ያለው ቢሆንም፣ የሚቃጠለው ሰልፈር ነበልባል የሚያብረቀርቅ ሰማያዊ ላቫ ምስልን የሚፈጥር ሲሆን በሌሊት ብቻ የሚታይ አስደናቂ ትዕይንት ነው ተብሏል፡፡
በኢቫን ስለሺ


__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
ምላሽ ይስጡ