በሱዳን በተከሰተው አዲስ የኮሌራ ወረርሽኝ ባለፈው ሳምንት 172 ሰዎች ሲሞቱ ከ2,500 በላይ የሚሆኑት በቫይረሱ መያዛቸውን የሀገሪቷ ባለስልጣናት አስታውቀዋል፡፡
በሱዳን ዋና ከተማ ካርቱም እና ኦምዱርማን ከተማ አብዛኛዎቹ ታማሚዎች መገኘታቸውን የገለጸው የአሶሼትድ ፕሬስ ዘገባ በሌሎችም የሀገሪቱ አካባቢዎች ሊዛመት ይችላል ብሏል፡፡
ድንበር የለሽ ዶክተሮች የታካሚዎች ቁጥር እየጨመረ በመምጣቱ መቋቋም አቅቷቸዋል ነው የተባለው፡፡
የኮሌራ ወረርሽኝ የጀመረው በግንቦት ወር አጋማሽ ላይ ሲሆን ባለፈው ሳምንት ብቻ ወደ 2,ሺህ የሚጠጉ የኮሌራ ተጠቂዎች መታከማቸው ተገልጿል፡፡
ብዙ ሕመምተኞች “ለመዳን በጣም ዘግይተው” በመድረሳቸው ህይወታቸው ማለፉን የጤና ባለሞያዎች የገለጹ ሲሆን የውሃ፣ የአካባቢ ጽዳትና የግል ንፅህና አጠባበቅ ላይ በስፋት መሰራት እንዳለበት አስገንዝበዋል፡፡
በመጋቢት ወር ድንበር የሌሽ የዶክተሮች ቡድን በሱዳን ነጭ ናይል ግዛት 92 ሰዎች በኮሌራ መሞታቸውንና ከየካቲት ወር መጨረሻ ጀምሮ 2,700 ሰዎች በበሽታው መያዛቸውን ገልጿል።
ምላሽ ይስጡ