ግንቦት 18 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) በሳዑዲ ዓረቢያ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የነበሩ 3 ሺህ 522 ኢትዮጵያውያን በዚህ ሳምንት ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል፡፡
በሳምንቱ ውስጥ በተደረገ 9 ዙር በረራ የተመለሱት 3218 ወንዶች እና 291 ሴቶች እና 13 ጨቅላ ህፃናት ሲሆን ከተመላሾች መካከል 308 እድሜያቸው ከአስራ ስምንት አመት በታች የሆኑ ታዳጊዎች ይገኙበታል።
በ4ኛው ዙር በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የሚገኙ ዜጎችን 50 ሺህ ዜጎችን ለመመለስ ታቅዶ ከመጋቢት 3/ 2017 በይፋ መጀመሩ ይታወቃል፤ በዚህም እስካሁን 35 ሺህ 876 ኢትዮጵያውያንን ወደ ሀገር መመለስ ተችሏል።
ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከሚመለከታቸው ባለድርሻና አጋር አካላት ጋር በመቀናጀት ለተመላሽ ዜጎች በአየር ማረፊያና በማቆያ ማዕከላት ተገቢውን ድጋፍ እና እንክብካቤ የማድረግ እና ከቤተሰብ ጋር የማቀላቀል ስራም በትኩረት እየሰራ ይገኛል፡፡
የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር
ምላሽ ይስጡ