በደሴ ሙዜም የተዘረፉ ቅርፆችን ለማሰባሰብና ሙዚየሙ ዘመኑን በዋጀ መልኩ በኢዲስ መልክ ለማደስ የኢትዮጵያ ቅርስ ባለአደራ ማህበር ከብሪትሽ ካውንስል ባገኘው 25 ሚሊዮን ብር ድጋፍ ሙዜሙ የሚታደሰበትን ፕሮጀት የካቲት 11/2015 ዓ.ም ይፋ መደረጉ ይታወሳል፡፡
በሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት ምክንያት ጉዳት እና ዘረፋ ደርሶበት የነበረው የደሴ ሙዚየም ከቀድሞ ይዞታው በተሻለ መንገድ ከግንቦት 23/2017 ዓ.ም ጀምሮ ለጎብኝዎች ክፍት እንደሚደግ የማህበሩ ዋና ሥራ አስኪጅ አቶ መቆያ ማሞ ተናግረዋል፡፡
ጦርነቱ ለሙዚየሙ መውደም ትልቁን ድርሻ የሚወስድ እንደሆነ የተናገሩት ዋና ሥራ አስኪያጁ ከዚያ በፊት በአየር ንብረት ለውጥ በተወሰነ ደረጃ ጉዳት ደርሶበት እንደነበረም አስታውሰዋል፡፡
የእደሳት ስራውን ለማከናወን ከታቀደው ገንዘብ በላይ እንደፈጀ አቶ መቆያ አንስተው ከግንቦት 23/2017 ዓ.ም ጀምሮ ለጎብኝዎች ክፍት ቢደረግም ከታህሳስ በኋላ ሙሉ ለሙሉ ለጎብኝዎች ክፍት እንደሚደረግና የጎብኝዎች ኪስ በማይጎዳ መልኩ የመግቢያ ክፍያ እንደሚኖረው ገልፀዋል፡፡
ከሙዚየሙ በጦርነቱ ምክንያት ከ4መቶ በላይ የጠፉ ቅርሶች በመኖራቸወ ሙዚየሙ ለጉብኝት ክፍት ከተደረገ በኋላም የተዘረፉ ቅርሶችን የማስመለስ ሥራ ይሠራል ያሉት ሥራ አስኪያጁ ማህበረሰቡ እና የሃይማኖት አባቶች ቅርሶቹን ለማስመለስ በሚደረገው ጥረት እንዲያግዙ ጠይቀዋል። ተመሳሳይ ቅርሶችን ከማህበረሰቡ በመፈለግ እና ከሌሎች ሙዚየሞች በማስመጣት ሙዚየሙን ሙሉ ለማድረግ እየተሠራ እንደሆነም ጠቁመዋል፡፡
ምላሽ ይስጡ