በዱክ ዩኒቨርሲቲ የሕክምና ማእከል የተመራ አዲስ ጥናት ሰዎችን ከሌሎች ዝርያዎች የሚለይ እና በአንጎል እድገት ላይ ወሳኝ ሚና የሚጫወት የዲ ኤን ኤ ክፍልን ለይቷል።
ይህ ልዩ የዲ ኤን ኤ ክፍል “HARE5” ተብሎ የተሰየመ ሲሆን በአንጎል ውስጥ አዳዲስ ነርቮችን በማፍራት እና አንጎልን በማስፋት ላይ ትልቅ ተጽዕኖ እንደሚያሳድር ተረጋግጧል።
ጥናቱ እንደሚያሳየው፣ በHARE5 ውስጥ ያሉ ትናንሽ ለውጦች እንኳን በአንጎል እድገት ላይ ከፍተኛ ለውጥ እንደሚያመጡ ነው። ይህም በአንጎል እድገት ላይ የሚከሰቱ ችግሮችን ለመረዳት እና ለማከም አዳዲስ መንገዶችን ሊከፍት ይችላል።
ሰዎች ከሌሎች እንስሳት በተለየ ትልቅ እና ውስብስብ የአንጎል ቅርፊት አላቸው።
ይህም ከፍተኛ የማሰብ ችሎታ እንዲኖራቸው አድርጓል።በዚህ ጥናት ውስጥ የተገኘው HARE5 በሰዎች ውስጥ ብቻ የሚገኝ ሲሆን በአንጎል እድገት ላይ እንደ ማስተካከያ (enhancer) ሆኖ ይሰራል ሲሉ የምርመራውን ውጤት አሳይተዋል።
ተመራማሪዎች በሙከራ አይጦች ላይ የተለያዩ የHARE5 ስሪቶችን በመጠቀም የእሱን ተፅእኖ ያጠኑ ሲሆን በሰው እና በቺምፓንዚ ሕዋሳት ላይ ምርምር አድርገዋል።
ውጤቱም እንደሚያሳየው ከሆነ የሰው ልጅ HARE5 በአይጦች እና በቺምፓንዚዎች ላይ ከሚገኙት ስሪቶች በተለየ መልኩ በአንጎል እድገት ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ እንደሚያሳድር ነው።
አዲሱ ግኝት በአንጎል እድገት ላይ የሚከሰቱ ችግሮችን እንደ አውቲዝም እና ስኪዞፈሪንያን ለመረዳት እና ለማከም ትልቅ እገዛ እንደሚያደርግ ተመራማሪዎች ጠቁመዋል።
በኢቫን ስለሺ
ምላሽ ይስጡ