የአገሪቱ ብሄራዊ መረጃና ደህንነት ኤጀንሲ በሂራን ክልል ኤል-ሀረሪ አካባቢ ማክሰኞ እና ረቡዕ ለሁለት ቀናት በደረሠው የዘመቻ ጥቃት 45 ‘የአሸባሪ ተዋጊዎች መሪ እና ሚሊሻዎች’ መገደላቸውን ገልጿል።
የሶማሊያ የጸጥታ ሃይሎች ከ2023 ጀምሮ በሞቃዲሾ የሞርታር ጥቃት ሲያደርሱ የነበረ ቡድን መሪን ጨምሮ 45 የአልሸባብ አሸባሪዎችን በሂራን እና የታችኛው ሸበሌ ክልሎች መግደላቸውን ትላንት ረቡዕ ባወጣው ይፋዊ መግለጫ አስታውቋል።
የብሔራዊ መረጃና ደህንነት ኤጀንሲ (ኒሳ) መግለጫ እንዳስታወቀው በሂራን ክልል ኤል-ሀሬሪ በተባለው አካባቢ ከማክሰኞ ከሰአት በኋላ እስከ እሮብ ስድስት የአየር ድብደባዎች ተካሂደው ሚሊሻዎችን ጨምሮ 45 የከዋሪጅ ተዋጊዎች መሪ ተገድለዋል ብሏል።
የሶማሊያ መንግስት ከአልቃይዳ ጋር ግንኙነት ያለው የአልሸባብ አሸባሪ ቡድንን ኸዋሪጅ ሲል ይጠራዋል።
አናዶሉን በስልክ ያነጋገራቸው የክልሉ የጸጥታ ባለስልጣን አቶ አህመድ መሀሙድ የስለላ መስሪያ ቤቱ ሰው አልባ አውሮፕላኖችን ተጠቅሞ ቡድኑና ከፍተኛ ኦፕሬተሮቹ ተደብቀው የሚገኙበትን ቦታ መትቷል ሲሉ አረጋግጠዋል።
ዘገባው በኦፕሬሽኑ የተገደሉት የአል-ሸባብ ከፍተኛ መሪ ከ2023 ጀምሮ በሞቃዲሾ ውስጥ የሞርታር ጥቃትን ሲፈፅም እንደቆዩ ገልጿል።
አልሸባብ ከ16 አመታት በላይ የሶማሊያ መንግስትን ሲዋጋ የቆየ፣ በመንግስት ባለስልጣናት እና ወታደራዊ አባላት ላይ በተደጋጋሚ ጥቃት እያደረሰ ያለ ቡድን መሆኑን ዘገባው ጠቅሷል።
__
ምላሽ ይስጡ