በአዲስ አበባ ከተማ ከሚገኙ መድኃኒት መደብሮች የመጠቀሚያ ጊዜ ያለፈባቸው መድኃኒቶችን ቀላቅለው ይዘው የተገኙና አላግባብ ያስቀመጡ 105 ተቋማት ላይ አስተዳደራዊ እርምጃ መወሰዱ ተገለጸ
የአዲስ አበባ ምግብ መድሃኒት ባለስልጣን በዘጠኝ ወራት በቻ በ1ሺ 600 በላይ የመድሃኒት መሸጫ ተቋማት ላይ የቁጥጥር ስራ መስራቱን ለጣቢያችን የገለጹት በአዲስ አበባ ከተማ ምግብ መድሃኒት ባለስልጣን የጤና ተቋማትና ባለሙያዎች ቁጥጥር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ገልገሎ ኦልጄራ ናቸው።
በተለይም የመሸጫ ተቋሙ የመድሃኒት አቀማመጥ ሁኔታና የመድሃኒት ግብዓቱ ጊዜ ያለፈበት መሆኑንና የቆይታ ጊዜውን በተመለከተ በተቀመጠው መመሪያ መሰረት ትክክለኝነቱ ላይ ቁጥጥር እንደሚደረግ ገልጸዋል፡፡
በዚህ መሰረትም በ9ወራት ብቻ በተደረገው ቁጥጥር ጊዜ ያለፈባቸው መድሃኒት የሸጡና አላግባብ መድሃኒቶቹን ያስቀመጡ 105 የመድሃኒት ተቋማት ላይ አስተዳደራዊ እርምጃ መወሰዱን ያነሱት ዳይሬክተሩ ከ105ቱ በ 30ው ላይ የማሸግና በ74ቱ ላይ የጽሁፍ ማስተንቀቂያ ብሎም በአንዱ ላይ ከገበያው ስርዓት የመሰረዝ እርምጃ መወሰዱን ገልጸዋል።
ባለስልጣን መስሪያቤቱ ከፌደራል ፖሊስ፣ ከአዲስ አበባ የጸጥታ ቢሮና ከኤሎችም የሚመለከታቸው አካላት ጋር በቅንጅት እየሰራ ነው ያሉት ዳይሬክተሩ ፤ አሁን ላይ ከከተማውና ከአገልግሎት መስጫ ተቋማቱ መስፋፋት ጋር የያይዞ የቁጥጥር ስራው በተቋማት ብቻ የሚሰራ ባለመሆኑ ህብረተሰቡም የቁጥጥሩ አካል ሊሆን ይገባል ሲሉ ጠቁመዋል፡፡
ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ከቁጥጥር ስራቱ ባሻገር የግንዛቤ ማስጨበጫውን ለማጠናከር የሚድያ ፎረም ማዋቀሩን የገለጹት ዳይሬክተሩ ፤ ከህብረተሰቡም የሚነሱ ቅሬታና ጥቆማዎችን ማስተናገድ የሚያስችል አማራጭ በማዘጋጀት እየሰራ መሆኑንም አመላክተዋል፡፡
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
ምላሽ ይስጡ