በየሆስፒታሉ የሚገኙና ህክምና ለማድረግ የሚመጡ ታካሚዎች የጨረር ምርመራን በተመለከተ በቂ ግንዛቤ የላቸውም ሲሉ ለመናኸሪያ የገለጹት በኢትዮጵያ ቴክኖሎጂ ባለስልጣን የጨረርና ኒኩለር ቴክኖሎጂ ሪጉላቶሪ ቁጥጥር ዳይሬክተር አቶ እሸቱ ጥላሁን ናቸው።
በተለይም እንደ ኤክስሬና ራጅ የመሳሰሉት የህክምና የምርመራ ሂደቶች እራሱን የቻለ መድሃኒት የሚመስላቸውና ካልታዘዘልን የሚሉ ታካሚዎች በርካቶች መሆናቸውን ገልጸው ፤እንደ ራጅና አልትራሳውንድ ያሉ የጨረር ህክምና ምርመራዎች የበሽታውን አይነትና ደረጃ ለማወቅ የምርመራ ሂደት ስለመሆናቸው በቂ ግንዛቤ የሌላቸው ታካሚዎች በርካታ መሆናቸውን ገልጸዋል።
በሌላ በኩል አላስፈላጊ የሆነ የጨረር ምርመራ በማዘዝ ገንዘብ የሚቀበሉ የህክምና ተቋማት መርካታ መሆናቸውን አንስተው የሚደረገውን ህክምናና ተገቢነት በተመለከተ የቁጥጥር ስራ ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ እየሰራ መሆኑን ገልጸዋል ።
ባለስልጣን መስሪያቤቱ ከውጪ የሚገቡ የጨረር አመንጪ መሳሪያዎች ትክክለኝነትና በአወጋገድ ዙሪያ ከሚሰራው የቁጥጥር ስራ ባለፈ ፤የግንዛቤ ማስጨበጥ ስራም እንደሚሰራ አንስተው እንደሃገር በሰዉ ጤናና በአከባቢም ላይ የሚኖረውን ብክለትም ለማስቀረትም የተለያዩ ስራዎች እየተከናወኑ መሆኑን አመላክተዋል፡፡
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
ምላሽ ይስጡ