ላለፉት ወራት በትግራይ ክልል የተፈጠረው የነዳጅ እጥረት ከፍተኛ የሆነ የኑሮ ውድነትና ተገቢ ያልሆነ መስተጓጎልን ሲፈጥር እንደነበር ይታወሳል፤ ይህንንም ተከትሎ ችግሩን ለመፍታት የክልሉ ንግድ ቢሮ በነዳጅ ማደያዎች ላይ ጥናት እያደረገ መሆኑን ለመናኸሪያ ሬዲዮ አስታውቋል፡፡
በክልሉ ያለውን የነዳጅ እጥረት ተገን በማድረግ በተለያዩ አካባቢዎችና የነዳጅ ማደያዎች ላይ ሰው ሰራሽ እጥረት እየተፈጠረ እንደሆነ የሚናገሩት የክልሉ የንግድ እና ኤክስፖርት ኤጀንሲ የንግድ ውድድር እና ሸማቾች ጥበቃ ዳይሬክተር አቶ ካሳሁን ክንደያ ናቸው፡፡
በክልሉ ለሆስፒታሎችና መሰል ፈጣን የነዳጅ አቅርቦት ለሚስፈልጋቸው ተቋማት በቅድሚያ እየተሰጠ ነው ወይ የሚለው የጥናቱ መነሻ እንደሆነ ዳይሬክተሩ አንስተው የአሰራር ለውጦችም እንደሚጠበቁ ተናግረዋል፡፡
በነዳጅ አቅርቦት ዙሪያ ከሰሞኑን መሻሻሎች ቢስተዋሉም ክልሉ ከሚያስፈልገው አንፃር በቂ የሚባል እንዳልሆነ አቶ ካሳሁን ገልጸዋል፡፡
ከዚህ በፊት ይገባ የነበረው ነዳጅ በቀን ከ7 እስከ 16 ቦቴ እንደነበር ዳይሬክተሩ ገልጸው፣ አሁን ላይ ከ1 እስከ 4 ቦቴ ያክል ብቻ በቀን እየገባ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ ከዚህ በፊት በክልሉ ሥም የወጡ ግን ክልሉ ላይ ያልደረሱ የነዳጅ ቦቴዎችን ጉዳይ ለባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ማመልከታቸውንም ዳይሬክተሩ አክለው ተናግረዋል።
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
ምላሽ ይስጡ