አሳምነው ስዩም ታምራት የተባለ የ40 ዓመት እድሜ ያለው ግለሰብ 1996 ዓ.ም የወጣውን የወንጀል ህግ አንቀፅ 627/1/፤/4/(ሀ) ላይ የተደነገገውን ህግ በመተላለፍ ተከሳሽ የግብረ ስጋ ግንኙነት ለመፈጸም በማሰብ ህዳር 11 ቀን 2017 ዓ.ም በግምት ከቀኑ 7፡00 በሚሆንበት ጊዜ ዐፄዘርዓያዕቆብ ክፍለ ከተማ አንድነት ቀበሌ የግል ተበዳይ ህፃን ዕድሜዋ 13 ዓመት ባልሞላት የ8 ዓመት ልጅ ጋር ከምትኖርበት መኖሪያ ቤት ውስጥ እጇን ይዞ ከአልጋ ላይ በማስተኛት ተበዳይ ስትጮህ አፏን በኃይል አፍኖ በመያዝ የግብረ ስጋ ግንኙነት የፈጸመባት በመሆኑ ዐቃቤ ህግ ክስ መስርቶበታል፡፡
ፍርድ ቤቱ ተከሳሽን በችሎት በማስቀረብ ማንነቱን ተጠይቆ ከአስመዘገበ በኋላ የዐቃቤ ህግ ክስ በችሎት ተሰጥቶት ቀሪው ክስ በችሎት ተነቦለት ክሱን በአግባቡ እንዲረዳው ከተደረገ በኋላ ስለ ክሱ ሁኔታ ተጠይቆ ክሱን አልቃወመውም ብሏል፡፡
ተከሳሽ የወንጀል ድርጊቱን አልፈጸምኩም ጥፋተኛ አይደለሁም በማለት ክዶ የተከራከረ ቢሆንም ዐቃቤ ህግ ይሰሙልኝ ያላቸውን ምስክሮች አቅርቦ አሰምቷል፡፡
ፍርድ ቤቱም የዐቃቤ ህግን ክስ፣የህክምና ማስረጃና የምስክሮችን ቃል ከመረመረ በኋላ ተከሳሽ በተከሰሰበት ድንጋጌ ሊከላከል ይገባል በማለት በወ/መ/ስ/ስ/ህ/ቁ/142/1/ መሰረት ፍርድ ቤቱ ትዕዛዝ የሰጠ ቢሆንም ተከሳሽ የቀረበበትን ክስና ማስረጃ የመከላከያ ምስክር በማቅረብ ማፍረስም ሆነ ማስተባበል አልቻለም፡፡
ፍርድ ቤቱም ተከሳሽ በተከሰሰበት ወንጀል ህግ አንቀጽ 627/1/፤/4/ሀ/ ላይ የተመለከተውን የህግ ድንጋጌ በመተላለፍ የግብረ ስጋ ድፍረት በደል ወንጀል በመፈጸሙ ጥፋተኛ ነው በማለት በወ/መ/ስ/ስ/ህ/ቁ/149/1 መሰረት የጥፋተኝነት ፍርድ ሰጥቷል፡፡
የደብረብርሃን ከተማ ወረዳ ፍርድ ቤትም ግንቦት 8 ቀን 2017 ዓ.ም ባስቻለው ችሎት ጠቅላላ የቅጣት ማቅለያና ማክበጃ ምክንያቱን ተቀብሎ የመረመረ ሲሆን 1 የቅጣት ማክበጃ ምክንያት እና 6 የቅጣት ማቅለያ ምክንያቶችን በመያዝ ተከሳሽን ያስተምራል፣ያርማል ሌሎችንም መሰል የወንጀል ድርጊት ፈፃሚዎችን ያስጠነቅቃል ሲል ከዚህ በፊት በዚሁ ጉዳይ በፖሊስ ጣቢያም ሆነ በማረሚያ ቤት የታሰረው ካለ በሚታሰብ ከግንቦት 8 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ በ13 ዓመት ጽኑ እስራት እና በወ/ህ/አ/123 መሰረት ከእስር ከተፈታ በኋላ በ2 ዓመት የወላጅነት መብት ከህዝብ አገልጋይ ከመሆንና ሞግዚት አስተዳዳሪ ከመሆን እንዲሻ ፍርድ ቤቱ እንደወሰነበት ከደብረብርሃን ከተማ አስተዳደር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
ምላሽ ይስጡ