ተያይዞም ሌላው የመሀል ተከላካይ ስፍራ ተጫዋች የሆነው ዊሊያም ሳሊባ በበኩሉ ተጨማሪ ምርመራዎች እንደሚደረጉለት ክለቡ አሳውቋል።
ዩሪየን ቲምበር ያለፉትን ወራቶች ከነጉዳቱ ሲጫወት እንደነበር ነው መረጃዎች የሚጠቁሙት ፤ ተጫዋቹ በተለይ ከአርሰናል ከ3 ሳምንት በፊት በአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ የፓሪስ ሴንት ጄርሜ የግማሽ ፍፃሜ የመልስ ጨዋታ በኋላ ቲምበር ሜዳ ላይ አልታየም።
አሁን ታዲያ ሲነዘንዘው የነበረውን የጉልበት ህመም ለመገላገል ትክክለኛው ሰአት ከመሆኑ ጋር በተያያዘ ቀለል ያለ ቀዶ ጥገና ለማከናወን መወሰኑ ተሰምቷል።
ተጫዋቹ ሁለገብ በመሆን በዚ አመት የግራም የቀኝም ተመላላሽ የተከላካይ መስመር ላይ በመጫወት ጥሩ ግልጋሎትን ሲሰጥ ቆይቷል ፤ የቀዶ ጥገናው ተጫዋቹ ለምን ያህል ጊዜ ያርቀዋል የሚለውን የጊዜ እርዝማኔ እርግጠኛ ሆኖ መናገር እንደማይቻል ተገልጿል።
የ23 አመቱ ተጫዋች አምና በመጣበት አመት የመጀመሪያ የፕሪሚየር ሊግ ጨዋታውን ከኖቲንጋም ፎረስት ጋር ሲያከናውን የጉልበት ጅማቱ ላይ በደረሰበት ጉዳት ከውድድር ዘመኑ ውጪ ሆኖ እንደነበር አይዘነጋም።
መድፈኞቹ የውድድር ዘመኑን ካጠናቀቁ በኋላ የተወሰኑ የእረፍት ጊዜያቸውን በሚገባ በመጠቀም ለቀጣዩ አመት የቅድመ ውድድር ዝግጅታቸውን በሲንጋፖር እና ሆንግ ኮንግ የሚያከኒውኑ ይሆናል።
በተያያዘ ዜና የቡድኑ የመሀል ተከላካይ መስመር ተጫዋች የሆነው ዊሊያም ሳሊባም ባሳለፍነው እሁድ በተደረገው የኒውካስል ዩናይትድ መርሀ-ግብር ላይ በመጀመሪያው አጋማሽ ላይ ባጋጠመው ህመም ሁለተኛው አጋማሽ ላይ አልታየም ነበር ፤ ታዲያ አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ ተጫዋቹ ተጨማሪ ምርመራን የሚጠይቅ ነገር እንዳጋጠመው አብራርቷል።

ምላሽ ይስጡ