የ22 አመቱ ጀርመናዊ የአጥቂ አማካኝ መስመር ተጫዋች በአሁን ሰአት ከሚፈለጉ ፤ በጣም አስደናቂ እንቅስቃሴን ከሚያደርጉ ተጫዋቾች ተርታ ስሙ ይሰለፋል።
ታዲያ ተጫዋቹን ለማስፈረም በጥብቅ ሁኔታውን ሲከታተሉ ከነበሩ ክለቦች መካከል አንዱ ማንቸስተር ሲቲ ነው ፤ የቤልጂየማዊው ኮኮብ ኬቨን ዲብሩይነ ተተኪ አልጋ ወራሽ እንዲሆን በማሰብ ይህንን ተጫዋች የማስፈረም ፍላጎት እንዳላቸው ሲገለፆ ቆይቷል።
ተጫዋቹን ለማስፈረም ፍላጎት ያላቸው ማንቸስተር ሲቲዎች ብቻ አይደሉም ሊቨርፑል እና ባየርሙኒክም ተጫዋቹን ለማስፈረም ፉክክር ውስጥ የሚገኙ ክለቦች መሆናቸውን ተከትሎ የፍሎሪያን ቪርትዝ የገበያ ዋጋ እየጨመረ መጥቷል።
በክለቡ ሌቨርኩዝን አማካኝነት ለዚህ ተጫዋች እየተጠየቀ የሚገኘው የዝውውር ሂሳብ እንዲሁም ጥቅማጥቅሙን ጨምሮ እስከ 300 ሚሊዮን ዩሮ ድረስ አንድ ክለብ ወጪ ማድረግ ይጠበቅበታል።
የፔፕ ጋርዲዮላው ቡድን ሲቲ የተጫዋቹን አቅም ቢረዱም የተጠየቀውን ዋጋ ያክል ወጪ የሚያስደርግ ክህሎት አለው ብለው ስለማያምኑ እና በአጠቃላይ የተጋነነ ዋጋ ነው በማለት ከፉክክሩ ውጪ መሆናቸውን አሳውቀዋል ሲል BBC ይዞት የወጣው መረጃ ያመላክታል።
የጋርዲዮላው ቡድን ሲቲ ከዚህ በፊት ፍሬድን ጨምሮ ጆርጂንሆ ፤ ፍራንኪ ዲዮንግ ዋጋቸው የተጋነነ ነው በማለት እነዚህን ተጫዋቾች ከማስፈረም መቆጠባቸው የሚታወስ ነው። በ2019 ግን የወቅቱ የባሎንዶር አሸናፊውን ሮድሪ ኸርናንዴዝን በማስፈረም አስደናቂ ዝውውር ማከናወናቸው የሚታወስ ነው።
ከዛ ውጪ በ2020 ከካሊዶ ኩሊባሊ እና ሀሪ ማጓየር ጋር ስማቸው በጣም በጥብቅ ሲያያዝ ሩበን ዲያዝን እንዲሁም ሀሪ ኬንን ከቶተንሀም ለማስፈረም ከጫፍ ደረሱ በተባለበት ሰአት ላይ ኤርሊንግ ሀላንድን ማስፈረም መቻላቸው የሚታወስ ነው።
አሁንም ቪርትዝ ላይ ያላቸውን ፍላጎት በማቀዝቀዝ ከፉክክሩ ራሳቸውን ማግለላቸውን ተከትሎ በ1ዐ ቁጥር ቦታ ላይ የቡድኑን የፈጠራ አቅም የመጨምር አቅም እና ክህሎት ያለውን ተጫዋች በገበያው ላይ አስሰው ማንን ያስፈርማሉ የሚለው ጉዳይ በቀጣይ እንዲጠበቅ ያደርገዋል።

ምላሽ ይስጡ