ይሄ ሀንጋሪአዊ በ2023 ሰኔ ወር ላይ በርንማውዝን ከተቀላቀለ በኋላ በጣም አስደናቂ የግል አቅሙን እያስመለከተ ይገኛል። በዛ ላይ ገና 20 አመቱ መሆኑም መዘንጋት መቻል የለበትም።
ስሙ በስፋት ከሊቨርፑል ጋር ሲያያዝ የቆየው የ21 አመቱ የግራ መስመር ተመላላሽ የተከላካይ ስፍራ ተጫዋች በበርንማውዝ ለተጨማሪ 3 አመት የሚያቆይ ውል ቢኖረውም በዚህ ክረምት ከክለቡ ጋር የሚለያይበት እድል ግን የሰፋ ስለመሆኑ ተገልጿል።
ተጫዋቹ ከራሱ አንደበት ወደ ትልቅ ክለብ ቢያመራ እንደማይጠላ መናገሩ እና በዋናነት ሊቨርፑሎች የአንዲ ሮቤርትሰን ተተኪ አልጋ ወራሽ የመሆን አቅም ያለው ተጫዋች ነው በሚል ኬርኬዥ ላይ ያላቸውን ፍላጎት እጅግ የጠነከረበት ሁኔታ ላይ መገኘቱ ይበልጥ ኬርኬዥ በቫይታሊቲ እንደማይቆይ ማረጋገጫ ነጥቦች ናቸው።
ሁለተኛው ጉዳይ ደግሞ ተጫዋቹ በማጥቃት እንቅስቃሴ ለቡድኑ የሚሰጠው ሚና እንዲሁም ከኳስ ውጪ ቦታውን በፍጥነት ተመልሶ በመያዝ በመከለከሉ ረገድ ለቡድኑ የሚሰጠው ትልቅ አስተዋጽኦ በተለያዩ ክለቦች እንዲፈለግ ምክንያት አድርጓታል።
ሶስተኛው ጉዳይ ኬርኬዝ በ2021/22 በAz alkmar ለመጀመሪያ ጊዜ ለዋናው ቡድን መጫወት ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ አንድም ጨዋታ በጉዳት ምክንያት አላመለጠውም። ስለዚህ ጉዳት ብዙ ጊዜ ማያጋጥመው ተጫዋች መሆኑም ሌላው ክለቦች ትኩረት እንዲያደርጉበት ያስገደደ ጉዳይ ነው።
አራተኛው ጉዳይ በቡድኑ ቴክኒካል ዳይሬክተር ሪቻርድ ሂውስ እና በቡድኑ የአማካኝ መስመር ተጫዋች ዶምኒክ ሶቦዝላይ ምክንያት ነው።
የሊቨርፑል ቴክኒካል ዳይሬክተር የሆነው ሪቻርድ ሂውስ ፤ ይህ ግለሰብ ተጫዋቹ አልካማርን ለቆ በርንማውዝን እንዲቀላቀል መንገዱን የዘረጋው ሰው ነው። ስለዚህ አሁንም ሊቨርፑልን እንዲቀላቀል መደላድሉን በመዘርጋት ረገድ ከሌሎች ክለቦች በተሻለ ፈጠን ብሎ እንዲንቀሳቀሱ ስለሚያስችለው ነው።
ሌላው ከዶምኒክ ሶቦዝላይ ጋር ያላቸው ቀረቤታ ነው። የሊቨርፑሉ አማካኝ በሀንጋሪ ብሄራዊ ቡድን አምበል እንደሆነ ይታወቃል። ስለዚህ ተጫዋቹን በማሳመን ወደ አንፊልድ እንዲያቀና ለማድረግ የተሻለ አቅም ስላለው ተጫዋቹ ወደ አንፊልድ ማቅናትን ምርጫው ሊያደርግ እንደሚችል ተገምቷል።
በእነዚህ 4 ጉዳዮች ምክንያት ሊቨርፑል ይህንን ዝውውር ከሌሎች ክለቦች በፈጠነ መልኩ እንዲያከናውኑ ያስችላቸዋል ተብሏል። የኬርኬዥ የዝውውር ኡደት ተጫዋቹን አንፊልድ እንደሚያደርሰው ይገመታል።
እንደ ዝውውሩ Expert ፋብሪዝዮ ሮማኖ ዘገባ ከሆነ ቀያዮቹ ከተጫዋቹ ጋር በግል ጥቅማጥቅሞች ጋር በተያያዘ ተነጋግረው ከስምምነት ላይ ደርሰዋል ሲል ዘግቧል። የአንዲ ሮቤርትሰንንም ቦታ በሚገባ ይተካል ተብሎ ታምኖበታል ፤ ቀያዮቹ ከወዲሁ በዝውውር መስኮቱ በንቃት እየተንቀሳቀሱ ይገኛሉ ፤ ከፍሪንፖንግ በመቀጠል የአርን ሽሎት ሁለተኛው ፈራሚ እንደሚሆን ይገመታል።

ምላሽ ይስጡ