በአማራ ክልል ባለፉት ዘጠኝ ወራት የተመረተ ከ20 ሺህ ኪሎ ግራም በላይ የኦፓል ማዕድን በማዕከላዊ ገበያ በኩል ለውጭ ገበያ መቅረቡን የክልሉ ማዕድን ሃብት ልማት ቢሮ አስታውቋል።
ለውጭ ገበያ ከቀረበው የኦፓል ማዕድን ምርት ከ7 ነጥብ 4 ሚሊየን ዶላር በላይ ገቢ መገኘቱን የቢሮው ኃላፊ ኃይሌ አበበ ተናግረዋል፡፡
በቀሪው ሩብ የበጀት ዓመትም እሴት የተጨመረበት የኦፓል ምርት ለማቅረብ ጥረት እየተደረገ ነው ተብሏል፡፡
በክልሉ ያለውን የማዕድን ሃብት በማልማት ከዘርፉ የሚገኘውን ገቢ ለማሳደግ የሀገር ውስጥና የውጭ ባለሃብቶችን በመሳብና በመደገፍ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ መሆኑን መናገራቸውን ኢዜአ ዘግቧል።
ከኦፓል ምርቱ በተጨማሪ 76 ኪሎ ግራም የወርቅ ምርት ለብሔራዊ ባንክ መቅረቡ የተመላከተ ሲሆን፤
ባለፈው በጀት ዓመት በክልሉ ተመርቶ በማዕከላዊ ገበያ በኩል ወደ ውጭ ከተላከው የኦፓል ምርት ከ2 ነጥብ 3 ሚሊየን ዶላር በላይ ገቢ መገኘቱን የክልሉ የማዕድን ሃብት ልማት ቢሮ መረጃ ያመለክታል።
__
ምላሽ ይስጡ