በዚህ መርሃግብር ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግስት ተቋማት የስራ ሀላፊዎች፣ ዲፕሎማቶች፣ የተለያዩ ድርጅት ሀላፊዎች፣ምሁራን፤ ተማሪዎችና ሌሎችም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ወደ ኮንቬንሽን ማዕከል መሰብሰቢያ አዳራሽ እየገቡ ናቸው።
በሁለተኛው ቀን የኤክስፖ ውሎ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ለአፍሪካ ትብብር እና ብልፅግና በሚል መሪ ቃል ይካሄዳል።
በዕለቱ በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ላይ የሚያተኩሩ ጥናታዊ ፅሁፎች እንደሚቀርቡና ቴክኖሎጂው የአፍሪካን መጻኢ እድል እንዴት እንደሚያንጽ የሚያመላክቱ ሀሳቦች ተነስተው ውይይት ይደረግባቸዋል ተብሎ ይጠበቃል።
በዚሁ ዕለት የተለያዩ ተቋማት እና ስታርታፖች ምርትና አገልግሎቶቻቸውን ለጉብኝት ያቀርባሉ።
ምላሽ ይስጡ