አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ለአፍሪካ ትብብር እና ብልፅግና” በሚል መሪ ሀሳብ እየተካሄደ ባለው ኤክስፖ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ተገኝተው ባደረጉት ንግግር፤ ኢትዮጵያ ባለፉት አምስት ዓመታት የቴክኖሎጂ አቅምና አጠቃቀምን ለማሳደግ በርካታ ሰርታለች ብለዋል። በዚህም አብዛኛው ህዝብ በተመጣጣኝ ዋጋ የብሮድባንድ እና የሞባይል አገልግሎት ማግኘት ችሏል ነው ያሉት።
AI ህልም ሳይሆን የተቋማት አንቀሳቃሽ ሞተር ነው ያሉት ጠ/ሚሩ፤በአህጉሩ የሰለጠነ የሰው ሀይልን በማፍራት ችግሮችን መፍታት ይገባል ብለዋል።
ኢትዮጵያ ከ5 ዓመታት በፊት በኤ.አይ ቴክኖሎጂ ፈር ቀዳጅ ሊያደርጋት የሚችለውን የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት አቋቁማ ወደ ስራ መግባቷን ያስታወሱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ኢንስቲትዩቱ አፍሪካ የቴክኖሎጂ ውጤቶች ተጠቃሚና ተከታይ ብቻ ሳትሆን በዘርፉ ተፅዕኖ ፈጣሪ ለመሆን አጋዥ መሆኑን አመላክተዋል።
አፍሪካ በሀገር በቀል የአርቴፊሻል ኢንተሊጀንስ የተመራ አካታች ብልጽግና በማምጣት የአጀንዳ 2063 ግቦችን ለማሳካት ወደ አዲስ ዘመን እየተሻገረች መሆኑንም አመላክተዋል።
ከ15 ሚሊዮን በላይ ኢትዮጵያውያን እና ነዋሪዎቿ የዲጂታል መታወቂያ መያዛቸውን እንዲሁም ክፍያዎችን ከጥሬ ገንዘብ ወደ ድጅታል መቀየር መቻሉን በመድረኩ አንስተዋል።
ምላሽ ይስጡ