አገልግሎቱ ይህን ያለው ትላንት ለመገናኛ ብዙሃን በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ነው፡፡ ለዘንድሮ የምርት ዘመን የሚገዛው የማዳበሪያ መጠን ካለፈው ዓመት አንጻር የ4 ነጥብ 6 ሚሊየን ኩንታል ብልጫ እንዳለው የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ተስፋሁን ጎበዛይ ተናግረዋል፡፡
መንግስት በአፈር ማዳበሪያ ዋጋ ላይ የ84 ቢሊየን ብር ድጎማ እንዳደረገ ያስታወቁት ሚኒስትር ዴኤታው፤ በአንድ ኩንታል ላይ ከ5ሺሕ ብር በላይ ድጎማ ተደርጓል ብለዋል፡፡
መንግስት ምርታማነትን ለማሳደግ ከማዳበሪያ በተጨማሪ የምርጥ ዘር አቅርቦት ላይ በትኩረት እየሰራ እንዳለም ሚኒስትር ዴኤታው አስታውቀዋል፡፡
በተያዘው በጀት ዓመት እስካሁን 1 ነጥብ 6 ሚሊየን ኩንታል ምርጥ ዘር መሰብሰቡን እና 400ሺሕ ኩንታል የሚሆነው ለአርሶ አደሩ መሰራጨቱን ገልጸዋል፡፡
በአትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ ተኪ ምርቶች ላይ በተሰራው ስራም 10 ነጥብ 34 ቢሊየን ዶላር የሚያወጣ ምርት በአገር ውስጥ መተካት እንደተቻለ ተናግረዋል፡፡
ባለፉት 3 ዓመታት አገራዊ እና ዓለም አቀፋዊ ሁኔታዎችን ከግምት ውስጥ ያስገባ የኢንደስትሪ ፖሊሲ ጸድቆ ወደ ስራ መግባቱን አስታውቀዋል፡፡
በተያዘው በጀት ዓመት የ9 ወራት አፈጻጸም በኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ ከ3 ነጥብ 1 ቢሊየን ዶላር በላይ ግምት ያለው ተኪ ምርት መመረቱን ሚኒስትር ዴኤታው አስታውቀዋል፡፡
ምላሽ ይስጡ