የኢትዮጵያ ቅርስ ባለስልጣን በመላ ሃገሪቱ ያሉ ቅርሶችን የነበረ ባህል፣ ታሪክና እሴታቸውን ሳይለቁ እንዲቆዩ ለማድረግ የቅርስ እደሳት ስራውን በስፋት እየሰራ መሆኑንና በተያዘው በጀት አመትም ከ 20 ያላነሱ ቅርሶችን ማደሱን ለጣቢያችን የገለጹት የባለስልጣኑ የቅርስ ጥበቃና ልማት መሪ ስራ አስፈጻሚ አቶ ሃብታሙ አብርሃ ናቸው።
ሃገሪቷ ያሏት ታሪካዊ ቅርሶች በሰው ሰራሽና በተፈጥሮ አደጋ ከሚደርሱባቸው ጉዳቶች በማደስ ለይታ በተሻለ መልኩ ሳቢ ከማድረግ አንጻር እየተሰራ ነው ሲሉ ገልጸው ፤ በድረዳዋ የሚገኘው የባቡር ጣቢያ ፣ በትግራይ ክልል የሚገኘው የአክሱም ሃውልትና የነገስታቱን መቃብር ስፍራን ጨምሮ ሌሎችም የረጅም አመታት የቆየ ታሪክ ያላቸውን ታሪካዊ ቅርሶችን አድሶ የማቆየት ስራዎ እየተሰሩ መሆኑን ያነሱት ስራ አስፈጻሚው፤ እንደሃገር በቅርስ ጥበቃና እድሳት ዙሪያ የሰለጠነ በቂ የሰው ሃይል አለመኖር ከውጪ ጠጋኞች እንዲመጡ እንደሚደረግና በዚህ የተነሳም በቀላሉ በየጊዜው የቅርስ እደሳትን ለማድረግ አዳጋች አድርጎታል ብለዋል፡፡
ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ በተለያዩ የሃገሪቷ ክፍሎች የሚገኙ ታሪካዊ ቅርሶችን እድሳት ለማድረግ አስፈላጊው ጥናት እንደሚደረግ ያነሱት ስራ አስፈጻሚው ፤ ለመታደስ በጥናት ላይ ያሉና እቅድ የተያዘባቸው አካባቢዎች መኖራቸውንም አክለው ተናግረዋል።
ምላሽ ይስጡ