በስራ ቅጥር ሽፋን በህገወጥ አለምአቀፍ የሰው አዘዋዋሪዎች ወደ ማይናማር ተወስደው ችግር ውስጥ የሚገኙ ዜጎችን ለመታደግ መንግስት እያደረጋቸው ያሉ ጥረቶች ቀጥለዋል።
ከሰሞኑ በህንድ ኒውዴልሂ የሚገኘው የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ኤምባሲ የልዑካን ቡድን ወደ ታይላንድ በመላክ በእስር ላይ ይገኙ የነበሩትን በ6 ዙር 459 ኢትዮጵያውያን ወደ አገራቸው እንዲመለሱ የተደረገ ሲሆን ይህም እንዲሳካ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ማናጅመንት ፣ በታይላንድ የኢትዮጵያ አየር ቢሮ እንዲሁም ግብረ-ሰናይ ድርጅቶች ከፍተኛ አስትዋጽዖ አድርጓል ተብሏል።
ኢትዮጵያውያንን በህክምና እና በኢንፎርሜሽንና ቴክኖሎጂ ዘርፍ ስራ ታገኛላችሁ በሚል የተሳሳተ መረጃ ወደ ታይላንድ ከዛም ወደ ማይናማር እየተወሰዱ ህገወጥ ስራዎችን እንዲፈፅሙ የሚደረጉ ሲሆን ለከፍተኛ የሰብአዊ መብት ጥሰት እየተዳረጉ ይገኛል ነው የተባለው።
ሕብረተሰቡ በሕገ ወጥ የሰዎች አዘዋዋሪዎች ሀሰተኛ ቅስቀሳ ተታሎ የሥራ ስምሪት ውል ወደ አልተፈጸመባቸው አገራት ከሚደረጉ እንቅስቃሴዎች እንዲቆጠብ ኤምባሲው አሳስቧል።
ምላሽ ይስጡ