አርሰናል ከአዲዳስ የትጥቅ አምራች ተቋም ጋር ባላቸው ስምምነት መሰረት በየአመቱ የክለቡን ታሪክ ፤ ማንነትን ሊያሳዩ የሚችሉ ዲዛይኖችን በመጠቀም ሁሌም አዲሱ የውድድር ዘመን ከመምጣቱ በፊት ይፋ እንደሚያደርግ ይታወቃል።
ታዲያ የቀጣይ አመቱ ማልያ ወደኋላ ተጉዞ የ1949/50 የውድድር ዘመንን ላይ ክለቡ ለመጀመሪያ ጊዜ የተጠቀመውን ማልያ መሰረት በማድረግ የተዘጋጀ ስለመሆኑ ተገልጿል።
ከዛ ውጪ አዳዲስ ቁጥሮችን የሚለብሱ ተጫዋቾች እንደሚኖሩም ለማወቅ ተችሏል። ግብ ጠባቂው ዴቪድ ሬያ የቡድኑ ቁጥር 1 ግብ ጠባቂ ስለሆነ 1 ቁጥርን ይረከባል። ራምስዴል በቋሚነት ክለቡን ለቆ ወደ ሳውዛምፕን ማምራቱን ተከትሎ ቁጥሩን ዴቪድ ሬያ ከቀጣይ አመት ጀምሮ በመረከብ የሚጠቀምበት ይሆናል። እንዲሁም ተስፈኛው ኤተን ንዋኔሪ አሁን ግብ ጠባቂው ዴቪድ ሬያ የሚለብሰውን 22 ቁጥርን የሚረከብ ይሆናል።
በቀጣይ በፕሪሚየር ሊጉ 37ኛ ሳምንት መድፈኞቹ በውድድር ዘመኑ በሜዳቸው የሚያደርጉት የመጨረሻ ጨዋታ የፊታችን እሁድ ከኒውካስል ዩናይትድ ጋር ያከናውናሉ ፤ ታዲያ በዚህ መርሀ ግብር ላይ ይህንን አዲሱን ማልያ ለብሰውት ወደ ሜዳ ይገባሉ ተብሏል።
ምላሽ ይስጡ