ጉግል በ Chrome ማሰሻው፣ በፍለጋ አገልግሎቱ እና በአንድሮይድ ኦፐሬቲንግ ሲስተም ላይ የማጭበርበር ተግባራትን ለመከላከል አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ (AI) መጠቀም መጀመሩን አስታወቀ።
የኩባንያው የጄሚኒ AI ሞዴል አካል የሆነ ስሪት በተጠቃሚዎች መሳሪያዎች ላይ በመስራት፣ በተለይም የኮምፒውተር ችግር እንዳለበት በመግለጽ ወደ ማጭበርበር የሚመሩ ድረ-ገጾችን በመለየት ለተጠቃሚዎች ማስጠንቀቂያ ይሰጣል።
ይህ እርምጃ የመጣው AI አጭበርባሪዎች በቀላሉ አሳማኝ የሆኑ የውሸት ይዘቶችን እንዲፈጥሩ እየረዳ ባለበት ወቅት ነው። ባለፈው አመት ብቻ በዓለም አቀፍ ደረጃ ከ1 ትሪሊዮን ዶላር በላይ በማጭበርበር ወንጀል እንደጠፋ የሚገልጹ መረጃዎች አሉ።
ጉግል ይህንን “የእርስ በእርስ መሻሻል ጨዋታ” ሲል የገለጸ ሲሆን፣ ወንጀለኞች AIን ሲጠቀሙ፣ የቴክኖሎጂ ኩባንያዎችም ወንጀሉን ለመከላከል AIን እየተጠቀሙ መሆናቸውን አመልክቷል።
በኢቫን ስለሺ
ምላሽ ይስጡ