በአውሮፓውያኑ 1994 በመፈንቅለ መንግስት ስልጣን ከያዙ በኋላ ሀገሪቱን ለ22 ዓመታት የመሩት ያሕያ ጃሜህ በ2017 በምርጫ ሲሸነፉ ሀገሪቱን ለቀው ወደ ኢኳቶሪያል ጊኒ ማምራታቸው ይታወሳል፡፡
በምርጫ ያሸነፉት ፕሬዝዳንት አዳማ ባሮ የጃሜህን በሙስና የተጨማለቀና በገንዘብ አባካኝነት የሚተች አመራር ለመመርመር ኮሚቴ ያቋቋሙት ወዲያው ነበር፡፡
ኮሚቴው በ2 ዓመታት ውስጥ ስራውን አጠናቆ የቀድሞው ፕሬዝዳንት 360 ሚሊየን ዶላር መዝረፋቸውን ይፋ አድርጎ ነበር፡፡
ይሁንና ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ የጃሜህ ቅንጡ ተሽከርካሪዎች የቁም እንስሳትና ጀልባዎችን ጨምሮ በርካታ ንብረቶችን በራሳቸው ስም ያዞሩና እጅግ በጣም ዝቅተኛ በሚባል ክፍያ የገዙ ባለስልጣናት እንዳሉ ይፋ ማድረግ ጀምረዋል፡፡
ይህን ተከትሎም ፕሬዝዳንት አዳማ ባሮው በባለስልጣናቱ ላይ ግልጽ ምርመራ ይደረጋል ብለዋል፡፡
በ2019 ከሚንስትሮች የተውጣጣ ግብረ ኃይል ያቋቋሙት ፕሬዝዳንቱ የጃሜህ ንብረት የሀገሪቱ ሀብት ነውና ገቢ የሚደረግበትን መንገድ እንዲያመቻች አድርገው ነበር፡፡
ጃሜህ በውጪ ሀገራት ጭምር ከፍተኛ ሀብት ያከማቹ ሲሆን የአሜሪካ መንግስት ብቻ በ2022 ቢያንስ 218 የተለያዩ ሀብቶችና 100 የግል አካውንቶቻቸውን እንዳገደባቸው ያስታወሰው ቢቢሲ ነው፡፡
ምላሽ ይስጡ