ኢትዮጵያ የከሰል ምርትን በስፋት ከሚጠቀሙ 5 ሀገራት አንዱዋ ስትሆን ምርቱን ለአለም አቀፍ ገበያ በከፍተኛ ደረጃ በማቅረብ የሚታወቁ 5 ሀገራት እንዳሉም ይገለጻል፡፡
የኢትዮጲያ አካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ዘመናዊ የሀይል አቅርቦት እጥረት ባሉባቸው ክልሎች የሀገር ውስጥ ኢኮኖሚን በማረጋጋት በኩል አስተዋጾ ያለው ምርት ሲሆን የማክሰል ሂደቱ ያልዘመነ፤በሳይንስ ያልተደገፈ፤ በህገ-ወጥ መንገድ በመሆኑ ብሎም በዘርፉ ያሉት አምራቾችም በእውቀት የተደገፉ ባለመሆናቸው የአፈር መሸርሸር ፤የደኖች መጨፍጨፍ ፤የካርበን ልቀተ መጨመር እናም የአየር ንብረት ለውጥ ማስከተሉ እየጨመረ መሄዱን ተጠቁሟል፡፡
የኢትዮጲያ አካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን የደን ልማት የደን ውጤቶች አጠቃቀም እና የህግ ተከባሪነት መሪ ስራ አስፈጻሚ አ/ቶ ቢተው ሽባባው ለመናኸሪያ ሬድዮ እንደገለጹት ከሰል የእንጨት ብክነትን መቀነስ ብሎም በርካታ ጥቅሞች ያሉት ቢሆንም ዘርፉ ከፍተኛ መነሻ ገንዘብ ስለማይጠይቅ በርካታ ሰዎች በባህላዊ መንገድ በዘርፉ እንደሚሳተፉ ገልጸዋል፡፡
ለከሰል ማክሰል የሚቃጠሉት ዕጽዋቶችም የተመረጡ ባለመሆናቸው የደን ሀብቱ የመመናመን ስጋት እንዳለበትም አመላክተዋል፡፡ አ/ቶ ቢተው አክለዉም በዘላቂነት የግብርና ግብዓቶችን ከሚጠበቀው በላይ መተካት እንደሚገባ አንስተዋል፡፡ በህገወጥ መልኩ የሚደረጉ የማክሰል ሂደቶችም ለተፈጥሯዊ አደጋዎች አጋላጭ በመሆናቸዉ ሳይንሳዊ አካሄድን መጠቀም የሚያስችሉ ስራዎች እየተሰሩ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡
የኢትዮጲያ አካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን የደን ሃብቱን ለመጠበቅ የተለያዩ ስትራቴጂዎችን በመቅረጽ እየሰራ መሆኑን አመላክቷል፡፡
ምላሽ ይስጡ