ከሰሞኑን የመገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎች መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎትን እንዲጎበኙት ተደርጓል፡፡
መናኸሪያ ሬዲዮ ያነጋገራቸው የመገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎች መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት በእቅድ ደረጃ የነበሩ ሃሳቦች በተግባር መሬት ላይ ወርደው የታዩበት፤ የሚያስመሰግን ስራ ነው ብለዋል፡፡
መሶብ በዋናነት በአገልግሎት አሰጣጥ ላይ የሚነሱ ቅሬታዎችን፤ ሙስናና ብልሹ አሰራሮችን ሙሉ ለሙሉ የሚያስቀር ከመሆኑ ባሻገር በየጊዜው በየመገናኛ ብዙሃኑ የሚዘገቡ የማህበረሰቡ ቅሬታዎችን የሚቀርፍ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
በቴክኖሎጂ የታገዘና ከወረቀት አሰራር የጸዳ በመሆኑ የህብረተሰቡን እንግልትና ምሬት ከመቅረፍም ባለፈ ያልተገባ ጥቅም ለማግኘት የሚንቀሳቀሱ አገልግሎት ሰጪዎች እንዳይኖሩ ያደርጋል ብለዋል፡፡
በመሶብ አገልግሎት ስር የተካተቱ አሰራሮች በቴክኖሎጂ የታገዙና የተሳሰሩ በመሆናቸው የሃገር ኢኮኖሚ ላይ ማነቆ የሆነው ሙስና እና ብልሹ አሰራርን ሙሉ በሙሉ የሚያስወግድ ነው ሲሉም ባለሙያዎቹ ተናግረዋል፡፡
የአንድ ማዕከል አገልግሎቱ የጊዜና የገንዘብ ብክነትን በማስቀረት የህብረተሰቡን እንግልት የሚቀርፍ ነውም ብለዋል፡፡
በሌላ በኩል አጠቃላይ በመሶብ የአንድ ማእከል የሚሰጠው አገልግሎት በኮምፒውተር የታገዘ በመሆኑ የተማረውን ወጣት የሰው ሃይል ከመጠቀም አንጻር አስጊ ነው፤ በቀጣይ አገልግሎቱ በመላው ሃገሪቱ ሲስፋፋ ስራ አጥ የሰው ሃይል ቁጥርን ሊጨምር ይችላል የሚል ስጋታቸውን አስቀምጠዋል።
12 ተቋማትን እና ከ46 በላይ ዋና ዋና አገልግሎቶችን በአንድ ማእከል ማግኘት የሚያስችለው ፕሮጀክት በቀጣይም በመላው ሃገሪቱ ቢስፋፋ አሁን ላይ ያለውን የአገልግሎት ተጠቃሚ ማህበረሰብ እንግልት የሚያስቀር መሆኑ በባለሙያዎቹ ተመላክቷል።
ምላሽ ይስጡ