በርካታ የእግርኳስ ቤተሰቦች የአለማችን ትልቁ የሀገራት የውድድር መድረክ የሆነው የአለም ዋንጫ በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ በአህጉራችን አፍሪካ ላይ እንዲከናወን ፊፋ እድሉን ለደቡብ አፍሪካ ሲሰጥ ከፍተኛ ተቃውሞ የገጠመው ጉዳይ እንደነበር የሚታወስ ነው።
አፍሪካ ይሄንን ትልቅ ውድድር እንዴት ታሰናዳለች ፤ አቅሙ እና በቂ ዝግጅትስ ያደርጋሉ ወይ የሚልም ጥያቄ ሲነሳ መቆየቱ አይዘነጋም። ደቡብ አፍሪካ ግን በ2010 በተሳካ መልኩ ውድድሩን በማሰናዳት መቼም ከማይረሱ የአለም ዋንጫ የውድድር መድረኮች ተርታ የሚሰለፍ አስደናቂ ዝግጅትን ማዘጋጀቷ የሚታወስ ነው።
አሁን ደግሞ በድብልብ ማርሻል አርት ክህሎት ያላቸው ተፋላሚዎች በየክብደት እርከኑ ተከፋፍለው የሚያከናውኑት የአለማችን ትልቁ የፍልሚያ መናኸሪያ ከሆኑ ተቋሞች መካከል አንዱ የሆነው Professional fighters league ወይም PFL አህጉራችን አፍሪካ ላይ እንደሚከናወን ይፋ ሆኗል።
PFL Africa የአወዳዳሪው አካል 3ኛ አለም አቀፍ የፍልሚያ መድረክ ሲሆን የፊታችን ሀምሌ ወር ላይ ደቡብ አፍሪካ ኬፕ ታውን ከተማ ግራንድ ዌስት አሪና ላይ እንደሚከናወን ተቋሙ በይፋ አሳውቋል።
የሊግ የውድድር ባህሪን የተላበሰው PFL ደቡብ አፍሪካ ላይ በሚያደርጋቸው ፍልሚያዎች በከባድ ሚዛን እንዲሁም በመካከለኛው ክብደት ላይ የተለያዩ ፍልሚያዎችን እንደሚያከናውን ይፋ አድርጓል።
PFL ፊቱን በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ አህጉራችን አፍሪካ ማዞሩ በሀገሪቱ ያለው የድብልቅ ማርሻል አርት ስፖርቱ በአጠቃላይ እንዲያድግ ፤ እንዲጎለብት እና አቅም እያላቸው ግን የመፋለሚያ የውድድር መድረክ ላጡ ተፋላሚዎች ምቹ መድረክ እንደሚሆንም ይታመናል።
ምላሽ ይስጡ