ሀብታሞች የሚጠቀሙበት እና ኢንቨስት የሚያደርጉበት መንገድ የሙቀት ማዕበል እና የድርቅ አደጋን በከፍተኛ ሁኔታ እንዲጨምር አድርጓል ሲሉ ተመራማሪዎች የአየር ንብረት ለውጥ ዙሪያ በተዘጋጀ ሳይንሳዊ መጽሔት ይፋ አድርገዋል።
ይህ የተጠናከረ የግል ሀብት በአስከፊ የአየር ንብረት ሁኔታዎች ላይ የሚያሳድረውን ተጽዕኖ ለመለካት የመጀመሪያው ጥናት ነው ተብሏል።
የኢቲኤች ዙሪክ የህዝብ ዩኒቨርሲቲ ሳይንቲስት ዋና ጸሐፊ ሳራ ሾንጋርት የበለጸጉ ግለሰቦችን የካርበን አሻራ በቀጥታ ከገሃዱ የአየር ንብረት ተጽእኖ ጋር እናያይዛለን” ሲሉ ለAFP የዜና ወኪል ተናግረዋል።
“ከካርቦን ሒሳብ ወደ አየር ንብረት ተጠያቂነት የሚደረግ ሽግግር ነው.” ያሉት ተመራማሪዎቹ ከዓለም አቀፉ አማካይ ዉጤት ጋር ሲወዳደር 1 በመቶዎቹ ሀብታም የሆኑት 26 እጥፍ ለአንድ መቶ አመት የሙቀት ማዕበል እና 17 እጥፍ በአማዞን ለተከሰተው ድርቅ አስተዋፅኦ አድርገዋል ሲል ጥናቱ አመልክቷል።
በቻይና እና በዩናይትድ ስቴትስ የሚገኙት 10 በመቶ ሃብታሞች የሚለቁት ልቀቶች – በአንድ ላይ ግማሹን የሚጠጋውን የአለም የካርበን ብክለትን ይሸፍናሉ።
እያንዳንዳቸው ከሁለት እስከ ሶስት እጥፍ የሙቀት ጽንፍ መጨመርን ማስከተላቸዉ ተመላክቷል።
ምላሽ ይስጡ