ከመንግስት ጋር የመድሃኒትና የህክምና ግብአቶችን ለማምረት ከስምምነት ለስራ ማስኬጃ የሚሆን ገንዘብ ባለመገኘቱ በታሰበው ልክ እንዳይሰራ ምክንያት መሆኑን የኢትዮጵያ የመድሃኒትና የህክምና መገልገያ አምራቾች ማህበር ለመናኸሪያ ሬዲዮ ገልጿል።
የኢትዮጵያ የመድሃኒትና የህክምና መገልገያ አምራቾች ማህበር ፕሬዝዳንት ዶክተር ዳንኤል ዋቅቶሌ፤መንግስት 123 የሚጠጉ የመድሃኒትና የህክምና መሳሪያዎች በሀገር ውስጥ እንዲመረቱ ከስምምነት ቢደረስም የስራ ማስሄጃ ገንዘብ ባለመመቻቸቱ በታሰበው መልኩ እንዳይሰራ አድርጎታል ብለዋል።
እንደ ሀገር ያለውን የመድሃኒት እጥረት ለመቅረፍ በዘርፉ የተሰማሩ ድርጅቶች ሰፊ ስራ እየሰሩ መሆኑን በመግልጽ አምራቾቹ ከባንኮች የብድር አገልግሎት ማግኘት ባለመቻላቸው ችግሩ ሊቀረፍ አለመቻሉን ተናግረዋል።
መድሃኒትና ህክምና መገልገያዎችን በተመለክተ አዲስ አዋጅ ወጥቶ መመሪያ እየተዘጋጀ መሆኑ ጠቁመዋል፡፡
የኢትዮጵያ መድሃኒት አቅራቢ ቦርድ ከኢትዮጵያ መድህን ድርጅት ጋር በመሆን የአማራቾች የኢንሹራንስ ዋስትና ለመቀበል በሂደት ላይ መሆናቸውን በመግልጽ በቀጣይ ሁለት ወራት የፋይናስ ችግሩን ለመፍታት ትልቅ ተስፋ የተጣለበት መሆኑን ተናግረዋል።
ምላሽ ይስጡ