ትውልዱም የሀገርን ዳር ድንበር በውል ማወቅና ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ጥቅም መከበር ውግንናውን ማሳየት እንዳለበት አስታውቀዋል፡፡
አባት አርበኞች ለኢትዮጵያ ብሄራዊ ጥቅም መከበር አሁንም በቁርጠኝነት ከመንግስት ጎን መሆናቸውን ነው ለመናኸሪያ ሬዲዮ የገለጹት፡፡
ሁሉም ኢትዮጵያዊ የተጀመረውን የባህር በር ጥያቄ ከመንግስት ጎን በመቆም ሊደግፈው እንደሚገባ እንዲሁም አሁን ያለው ወጣቱ ትውልድም ለዳር ድንበሩ መከበርና የሀገር ሉዓላዊነት ትኩረት መስጠት እንዳለበት አስረድተዋል፡፡
በተለያየ መስክ ለሀገር መስዋትነት የከፈሉ አርበኞች ተገቢው ክብር ሲሰጣቸው፤ ተተኪ የዘመኑን አርበኛ ማፍራት ስለሚቻል መንግስት ለጉዳዩ ትኩረት እንዲሰጥ ሲሉም አባት አርበኞቹ ጠይቀዋል፡፡
የባህር በር ጉዳይ ባለፉት በርካታ ዓመታት “የእግር እሳት ሁኖብን ቆይቷል” ያሉት አርበኞቹ፤ አሁን ላይ መንግስት በግልጽ ጥያቄ በማቅረቡና ትኩረት በመስጠቱ እጅግ ደስ አሰኝቶናል ብለዋል፡፡
በመሆኑም መንግስት በሚፈልጋቸው ቦታ ሁሉ በመገኘት አስፈላጊውን ድጋፍ ለማድረግ ቁርጠኛ መሆናቸው አስታውቀዋል፡፡
አሁን ላይ የኢትዮጵያን የዘመናት ጥያቄ ለማስከበርና የባህር በር ባለቤት ለመሆን የተለያዩ ስራዎች እየተሰሩ መሆኑ የተገለጸ ሲሆን፤ ሁሉም ዜጋ በተለይም ወጣቱ የሀገርን ብሄራዊ ጥቅም በውል በመገንዘብ አጀንዳውን ሊደግፈው እንደሚገባ ተመላክቷል፡፡
ምላሽ ይስጡ