ዘንድሮ ለ84ኛ ጊዜ የሚከበረውን የአርበኞች ቀንን ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት ፋሽስተ ኢጣሊያን በስተመጨረሻ በተሸነፈበት ቦታ ለማክበር ዝግጅቱን ማጠናቀቁን የኢሉ አባበር ዞን ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ለመናኸሪያ ሬዲዮ አስታውቋል፡፡
የዞኑ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ አቶ ወንድሙ ደበላ ለረጂም ጊዜያት ቦታው ትኩረት በማጣቱ ትውልዱ ቀኑና ቦታው ሳያቅ መቆየቱን በማመላከት ዘንድሮ በዞኑ ለሦስተኛ ጊዜ ለሚከበረው ክብረ በዓል የፓናል ወይይትን ጨምሮ የተለያዩ እንቅስቃሴዎች እየተደረጉ መሆናቸውን አመላክተዋል፡፡
በዘንድሮ ከብረ በዓል በተለይም አባት አርበኞች ፋሽስቱ ኢጣሊያንን ድል የነሱበትን የሳምቤ ተራራ አከባቢን በማልማትና አከባቢዉ ላይ ያለዉን ድልድይ በዘመናዊ መልኩ በመቀየር ተንጠልጣይ የብረት ገመድ ድልድይ ተሰርቶ ስላለቀ በእለቱ ይመረቃል ተብሎ እንደሚጠበቅ አመላክተዋል፡፡
ጎሬ በ1928 ዓ.ም በሁለተኛው የፋሺስት ጣልያን ወረራ ምክንያት የኢትዮጵያ ዋና ከተማ ሆና ተመረጣ የኢትዮጵያ ዋና ከተማ ሆና መቆየቷ ይታወቃል፡፡
ምላሽ ይስጡ