የአዲስ አበባ ከተማ ጤና ቢሮ በቀጣይ ከግንቦት 6 እስከ 15 ቀን 2017 ዓ.ም የሚካሄደውን የኩፍኝ ክትባት ዘመቻ በተመለከተ ከሚዲያ አካላት ጋር ውይይት እያካሄደ ነዉ፡፡
በህፃናት ላይ በስፋት የሚከሰተው የኩፍኝ በሽታ ወረርሽኝ ለመከላከል ዘመቻዉ እንደሚደረግ የአዲስ አበባ ጤና ቢሮ የክትባት ፕሮግራም አስተባባሪው አቶ ሙሉቀን ተስፋዬ ገልፀዋል።
ለኩፍኝ በሽታ በሃገራችን በመደበኛነት ክትባቱን ለ45 አመታት አካባቢ ሲሰጥ የቆየ ቢሆንም ነገር ግን በሽታው በተለያዩ ሃያላን በሚባሉ ሃገራትም ከፍተኛ ሁኔታ ሲስፋፋ እንደነበር ገልፀዋል።
በአለም ላይ የኩፍኝን በሽታ ለማከም የተረጋገጠ መድሃኒት እንደሌለው የሚገልፁት አቶ ሙሉቀን አስቀድሞ መከተብና ወደ ጤና ተቋም መሄድ ከተቻለ መከላከል እንደሚቻል አመላክተዋል።
በሽታው በዋናነት በቫይረስ መልኩ የሚዛመት በመሆኑ የተረጋገጠ መድሃኒት አለመኖሩ ለሳንባ ምች፣ ለአደገኛ ተቅማጥ እና እንዲሁም ለመተንፈሻ አካላት ህመም የማጋለጥ እድሉ ከፍተኞ ነው ብለዋል።
የኩፍኝ በሽታ ከ0.1 እስከ 10 በመቶ የመግደል ሃይል ያለው ሲሆን እንደኛ ባሉ ግጭቶች ባሉባቸው ሃገራት ግን እስከ 30 በመቶ እንደሚገድል አቶ ሙሉቀን አመላክተዋል።
ዘመቻውን ማካሄድ ያስፈለገው በየአመቱ የሚደረገው የጥናት ትንተና እየጨመረ በመሆኑ እንደሆነ ገልፀዋል።
በቀጣይ የሚዲያ አካላት፣ የጤና ባለሙያዎችና ሌሎችንም የሚመለከታቸውን አካላት በማሳተፍ እንደ አዲስ አበባ ከተማ ዘመቻውን እንደሚጀምሩ ተናግረዋል።
ምላሽ ይስጡ