በአውስትራሊያ አንድ የሬዲዮ ጣቢያ ከአድማጮች “የፕሮግራም አዘጋጇ ማንነት ጥያቄ አስኪያስነሳ ድረስ በሚስጥር ለ6 ወራት ያህል ጊዜ በAI የተፈጠረች ሴት አስተናጋጅን መጠቀሙ ክስ አስነስቶበታል።
በሲድኒ ውስጥ የሚያሰራጨው የአውስትራሊያ ሬዲዮ ኔትወርክ Thy የምትባል አዲስ የፕሮግራም አቅራቢ አስተዋውቋል፤ የፕሮግራም አቅራቢዋም “የሥራ ቀናችሁን ከ Thy ጋር” የሚል ፕሮግራም ተቀርጾላት እርሱን እየመራችም ቆይታለች፡፡
ወጣቷ የሬዲዮ ፕሮግራም አዘጋጅ ከሰኞ እስከ አርብ በቀን ለ4 ሰዓት ሙዚቃ ታቀርባለች፡፡ አድማጮች ስለ ሚስጥራዊዋ የሬዲዮ ፕሮግራም አዘጋጅ ጥያቄዎች መጠየቅ እስኪጀምሩ ድረስ ነገሮች ያለችግር ቀጥለው ነበር ያለው የኦዲቲ ሴንተራል ዘገባ ነው።
የአባት ስም የሌላት እና በየትኛውም የማህበራዊ ድረ-ገጽ ምንም አይነት የህይወት ታሪክ ያልነበራት አዘጋጇ በቂ አጠራጣሪ ነገሮችም ይገኙባታል፤ አንዳንድ አድማጮችም የምትጠቀማቸው ቃላት እና ሀረጋት ድግግሞሽ ያሏቸው በመሆኑም ጥርጣሬያቸውን ከፍ አድርጓል፡፡
ይህን ተከትሎም የእርሷን እውነተኛ ማንነት በርካቶች በተደጋጋሚ መጠየቃቸውን ተከትሎ የሬዲዮ ጣቢያው በመጨረሻ እውነተኛ ሰው እንዳልነበረች አስታውቋል።
የአውስትራሊያ ሬዲዮ ኔትዎርክ ፕሮጀክት መሪ ፋይድ ቶህሜ ሚስጥራዊዋ የሬዲዮ ፕሮግራም አቅራቢ ትክክለኛ ሰው ሳትሆን በAI የበለጸገ አፕሊኬሽን መሆኑን አረጋግጠዋል፡፡
በአገሪቱ የሬዲዮ ጣቢያዎች በስርጭት ወቅት በAI የተቀነባበሩ ይዘቶችን እንዳይጠቀሙ የሚከለክሉ ህጎች ባይኖሩም፣ የሬዲዮ ጣቢያው AI ሲጠቀም ባለማሳወቁ እና አድማጮች የፕሮግራም አዘጋጇ እውነተኛ ሰው ናት ብለው እንዲያስቡ በማድረጉ ተችቷል።
ምላሽ ይስጡ