በ1992 ዓ.ም የተቋቋመው አዲስ ህይወት አጠቃላይ ሆስፒታል የተለያዩ የጤና አገልግሎቶችን በመስጠት 25 ዓመታትን ያስቆጠረ ሲሆን የህክምና አሰጣጥ ጥራቱን በማሻሻል አሁን ላይ በዘመናዊ የህክምና መሳሪዎች እንዲሁም ከ 1ሺህ በላይ የጤና ባለሙያዎችን በመያዝ እየሰራ እንደሚገኝ ተገልጿል።
ሆስፒታሉ ከተቋቋመበት ጊዜ አንስቶ የነበሩ ተግዳሮቶችን በመቅረፍ ከጊዜ ወደ ጊዜ አገልግሎት አሰጣጡን እያዘመነ ለታካሚዎች ምቹ የህክምና አገልግሎት እየሰጠ መሆኑን በዛሬው ዕለት ባከበረው 25ኛ ዓመት ክብረ በዓሉ ላይ ገልጿል።
ምላሽ ይስጡ