👉ሁለቱ ቡድኖች የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግን ካሳኩ 10 አመት እና ከዛ በላይ ያስቆጠሩ ቡድኖች ናቸው።
የ2010 የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግን በልዩው ሰው The special One ከፖርቹጋላዊው አሰልጣኝ ጆዜ ሞሪንሆ ጋር በመሆን ከፍ አድርገው ካሳኩ በኋላ ድጋሜ እዚ መድረክ ላይ ዋንጫውን ማሳካት አልቻሉም። ቡድኑን አሁን በሚያሰለጥነው ጣልያናዊው ታክቲሺያን ሲሞኒ ኢንዛጊ ስር ከአንድ አመት በፊት አታቱርክ ላይ የፍፃሜ ተፋላሚ መሆን ቢችሉም በማንቸስተር ሲቲ 1-0 በሆነ ጠባብ ውጤት ተረተው ከዋንጫው ውጪ መሆናቸው የሚታወስ ነው።
ታዲያ ዳግም ለፍፃሜው ለመብቃት ካለላቸው ደግሞ ይሄንን ዋንጫ ከ15 አመት በኋላ ለማሳካት ከፍተኛ ጥረት እያደረጉ ይገኛሉ። ለ3ዮሽ ዋንጫ ሲንደረደር የነበረው ይህ ቡድን በ2 ሳምንት ውስጥ በውጤት እጦት በመፈተን በሴሪያው መሪነታቸውን ለናፖሊ አስረክበው ፤ በኮፓ ኢታሊያ ደግሞ በከተማ ተቀናቃኛቸው ኤሲ ሚላኖች ከውድድሩ ተሰናብተው ነው ወደ ስፔን የሚያቀኑት።
በሀንሲ ፍሊክ የሚመሩት የካታሎኑ ቡድን ባርሴሎና በ2015 የሊዮኔል ሜሲ ፤ ኔይማር ጁኒየር እና ልዊስ ሱዋሬዝን ጥምረት ሊያስታውሱ የሚችሉ ለተመልካች እጅግ አዝናኝ ለተጋጣሚ ደግሞ እጅግ የሆነ አጥቂ ጥምረትን የፈጠሩት ራፊንሀ ፤ ላሚን ያማል እና ሌዋንዶውስኪ በአውሮፓ በርካታ ጎሎችን ያዘነበ የአጥቂ ጥምረት ነው።
ቡድኑ የ3ዮሽ ክብርን ለመጎናፀፍ 7 ጨዋታ ብቻነው የሚቀረው። የኮፓ ዴል ሬ ዋንጫን የምንጊዜም ባለአንጣቸው ሪያል ማድሪድን 3-2 በማሸነፍ ማሳካታቸው የሚታወስ ሲሆን ላሊጋውንም በ4 ነጥብ ልዩነት እየመሩ ይገኛሉ ፤ ጀርመናዊው አሰልጣኝ ሀንሲ ዲተር ፍሊክ ቡድኑን ያዋቀሩበት መንገድ እያስወደሳቸው ይገኛል ፤ አሰልጣኙ እስካሁን ለፍፃሜ በበቃባቸው 7 አጋጣሚዎችን ሁሉንም በማሸነፍ የፍፃሜ ጨዋታ ላይ ከጆዜ በመቀጠል ጥሩ ሪከርድ ያለው አሰልጣኝ መሆኑን እያሳየ ይገኛል። ዛሬ በሜዳቸው በስታዲዮ ልዊስ ኮምፓኜስ ስቴዲየም ላይ የሚያደርጉት የመጀመሪያ ዙር እና በቀጣይ ማክሰኞ የመልሱን ጨዋታ በማሸነፍ በድምር ውጤት ለፍፃሜው መብቃታቸውን ካረጋገጡ ዋንጫውንም የማሳካት እድላቸው ሰፊ እንደሚሆን ተገምቷል።
ቡድኑ የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ የዋንጫ ክብርን ለመጨረሻ ጊዜ ያሳካው አስደናቂ በነበረው የኔይማር ጁኒየር ፤ በሊዮኔል ሜሲ እና ልዊስ ሱዋሬዝ ጥምረት ታግዘው በ2014/15 የውድድር ዘመን ላይ እንደነበር አይዘነጋም ፤ ታዲያ ከ11 አመታት በኋላ በላሚን ያማል ፤ ራፊንሀ እና ሌዋንዶውስኪ ደጋፊዎቹ የናፈቁት ይህ ዋንጫ በዘንድሮው አስደናቂው የሀንሲ ፍሊክ ቡድን ይሳካ የሚሆን ጉዳይ ይጠበቃል።
አሰልጣኝ ሲሞኒ ኢንዛጊ የወቅቱ የአለማችን ምርጡ ቡድን ባርሴሎና ነው ሲሉ ለዛሬ ተጋጣሚአቸው ያላቸውን አክብሮት አሳይተዋል።
ኦፕታ አናሊስት ለዛሬውን ጨዋታ ባርሴሎና 52 በመቶ የማሸነፍ እድል አለው ሲል ተንብየዋል።።
ጨዋታው ምሽት 4:00 ይጀምራል ፤ ፈረንሳዊው ዳኛ ክሌመንት ተርፒን ደግሞ በመሀል አልቢትርነት ጨዋታውን የሚመራው ይሆናል።

ምላሽ ይስጡ