የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ኢትዮጵያ ታምርት በተሰኘው ንቅናቄ 288 ተሳታፊዎች ያሉት ከ6ሺህ በላይ የግብይት ትስስር የሚፈጥር ኤክስፖ ለ3ተኛ ጊዜ ከሚያዚያ 25 እስከ 29/2017 ዓ/ም ለ5 ተከታታይ ቀናት በአዲስ ኮንቬንሽን ማዕከል ሊካሄድ መሆኑ ገልጿል፡፡
በኤክስፖው 4 ሚሊየን ብር የሚገመት ግብይት ሊከናወን እንደሚችል ተገምቷል፡፡
የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ሚኒስትር አቶ መላኩ አለበል በዚሁ ወቅት እንደተናገሩት ከውጪ የሚገቡ ምርቶችን በሀገር ውስጥ ተኪ ምርቶች ለመተካት በተጀመረው ሂደት ማህበረሰቡ የሀገር ውስጥ ምርትን ተጠቃሚ እንዲሆን ሰፊ ስራ ተሰርቷል ብለዋል፡፡
ኤክስፖው የምርቶቸን የጥራት ደረጃ እና የአምራቾችንም አቅም የሚያሳይ መሆኑን የገለጹት ሚኒስትሩ፤ ከዚህ ቀደም ከነበሩት ኤክስፖዎች በበለጠ ከክልል አምራች ኢንዱስትሪዎችን በማሳተፍ ለየት ለማድረግ እንደተሞከረ አስታውቀዋል፡፡
በፕሮግራሙ 161 ከፍተኛ ኢንዱስትሪዎች፤ 101 አነስተኛ እና መካከለኛ ኢንዱስተሪዎች፤ 17 አዳዲስ ልዩ የፈጠራ ስራዎች፤ 4 ከአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን እንዲሁም ሌሎችም እንደሚሳተፉበት ገልጸዋል፡፡
በኤክስፖው በ4 አጀንዳዎች ለኢንዱስሪዎች አመቺ የሆኑ ፖሊሲዎችን ለመቅረጽ፤ በማኒፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪው እሴት የተጨመረባቸው ምርቶችን ለአለም አቀፍ ገበያ ማቅርብ እንዲሁም አነስተኛ እና መካከለኛ ኢንደስትሪዎች በዘርፉ የሚያጋጥማቸውን ተግዳሮቶች መቅረፍ ብሎም አገልግሎቶችን ከሎጀስቲክ ጋር በማስተሳሰር ገበያውን ተደራሽ ማድረግ በሚቻልባቸው ጉዳዮች ዙሪያ የፓናል ውይይት እንደሚደረግ ጠቁመዋል፡፡
__
ምላሽ ይስጡ