የኢትዮጵያ ሰራተኛ ማህበራት ኮንፌዴሬሽን /ኢሰማኮ/ በአንዳንድ ተቋማት ስር የሚገኙ አሰሪዎች ለሰራተኞቻቸው ጥብቅና በመቆማቸው ብቻ ከስራ ገበታቸው የመፈናቀል አደጋ እያጋጠማቸው መሆኑን ተመልክቻለሁ ሲል አስታውቋል፡፡
የኮንፌዴሬሽኑ ፕሬዝዳንት አቶ ካሳሁን ፎሎ በተቋማት ደረጃ ያሉ አሰሪዎችም ሆኑ የማህበሩ ኃላፊዎች ለአባላቶቻቸው መብት መከበር ስለሞገቱ ብቻ ከስራ የመባረር፤ የማዋከብ፤ አለፍ ሲል ደግሞ ከነበሩበት የስራ ቦታ የማዘዋወር ቅጣት እየደረሰባቸው ነው ብለዋል፡፡
ፕሬዝደንቱ ለመብት መከበር የሚሞግቱ ሰራተኞች እስር እና እንግልት እየደረሰባቸው እንዳለ መረጃዎች እንደሚደርሳቸው ጠቁመው፤ በተለይ ከፋብሪካዎች በተደራጀ መልኩ ጥሪ እና ጥቆማ እንደሚደርሳቸው ነው የገለጹት፡፡
በዚህም ኮንፌዴሬሽኑ በተደራጁ መዋቅሮች ስር በሰራተኞች ላይ የሚደርሰውን እስርም ሆነ እንግልት ለመቅረፍ ዘርፈ ብዙ ስራዎችን እንደሚሰራ አስታውቀዋል፡፡
የኢትዮጵያ ሰራተኛ ማህበራት ኮንፌዴሬሽን /ኢሰማኮ/ በተለያዩ ጊዜያት የሚጠየቁ የሰራተኞችን የመብት ጥያቄዎች ለማስመለስ መሞገቱን እንደሚቀጥል ፕሬዝዳንቱ አስታውቀዋል፡፡
ምላሽ ይስጡ