ማርክ ካርኔይ እና ሊብራል ፓርቲ በካናዳ ምርጫ ድል እንደቀናቸው የተናገሩ ሲሆን፣ የዶናልድ ትራምፕ አቋም ለውጤቱ እንዳገዛቸው ተገልጿል።
የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ወደ ሥልጣን ከመጡበት ጥር ወር ጀምሮ የጎረቤት አገር የሆነችው ካናዳን 51ኛዋ የአሜሪካ ግዛት እንደምትሆን በተደጋጋሚ ሲናገሩ እንደነበር ይታወሳል፡፡
ይህም ሊብራል ፓርቲው በምርጫው እንዲያሸንፍ እንደረዳው የተገለጸ ሲሆን፤ ዶናልድ ትራምፕ ይህንን አቋማቸውን ይፋ ከማድረጋቸው በፊት የወግ አጥባቂው ተወዳዳሪ ፒር ፖሊየቭ ያሸንፋሉ ተብሎ ይገመት እንደነበር ተመላክቷል፡፡
አገሪቱ ላለፉት አስርት ዓመታት የመሩት የሊብራሉ ፓርቲ አባሉ ጀስቲን ትሩዶ የአገሪቱ ኢኮኖሚ ላይ ምንም ለውጥ ባለማሳየታቸው በፓርቲው ደጋፊዎች ዘንድ ቅሬታ ተፈጥሮ ነበር።
የካናዳ ሊብራል ፓርቲ አገሪቱን ለረዥም ዓመት ያስተዳደሩትን ትሩዶን አስወግዶ የባንክ ባለሙያ የሆኑትን ማርክ ካርኔ መሪው አድርጎ ከመረጠ በኋላ “አስደናቂ” የተባለውን የምርጫ ውጤት ማግኘቱን ቢቢሲ አስነብቧል፡፡
ምላሽ ይስጡ