አጥናፉ እሸቴ የተባለው ተከሳሽ ሰውን ለመግደል በማሰብ መስከረም 14 ቀን 2016 ዓ.ም ከቀኑ በግምት 10፡00 ሰዓት ሲሆን በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 02 ሙሉ ሸዋ ስጋ ቤት ተብሎ ከሚጠራው አካባቢ ተከሳሽ ሟች ታመነ ክፈተውን በመሳደቡ በተነሳ ፀብ ሟችን አንገቱን አንቆ በመያዝ በደረሰበት ጉዳት ምክንያት ህይወቱ በእለቱ እንዲያልፍ አድርጓል ነው የተባለው።
በፍትህ ሚኒስቴር የጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ዘርፍ የልዩ ልዩ ወንጀል ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ዐቃቤ ሕግ በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 1ኛ ሰው ግድያና ከባድ ውንብድና ወንጀል ችሎት በፈፀመው ተራ ሰው መግደል ወንጀል ክስ አቅርቦበት ክርክር ሲደረግ ቆይቷል፡፡
በክርክሩ ሂደትም የዐቃቤ ሕግ ማስረጃ ከተሰማ በኋላ ተከሳሽ እንዲከላከል ብይን ተሰጥቶ የመከላከያ ምስክሮችን በማቅረብ ያሰማ ቢሆንም የቀረበበትን ክስ ሊከላከል ባለመቻሉ ፍርድ ቤቱ በተከሳሽ ላይ የጥፋተኛነት ፍርድ በመስጠት በ7 ዓመት ፅኑ እስራት እንዲቀጣ ሲል መወሰኑን ከፍትህ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ምላሽ ይስጡ