የኮቪድ 19 ወረርሽ ዓለም ላይ በተከሰተበት ወቅት በሽታውን ለመግታት መገናኛ ብዙሃንን ጨምሮ በርካታ ያደረጉት ርብርብ ውጤት ማስመዝገቡን ብዙዎች ይስማሙበታል፡፡
የመንገድ ደህንነትና መድን ፈንድ አገልግሎት አስከፊነቱ የቀጠለውን የትራፊክ አደጋ ለመከላከል ሁሉም አካላት የበኩላቸውን ሚና እንዲወጡ ጠይቋል፡፡
የመንገድ ደህንነትና መድን ፈንድ አገልግሎት ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ጀማል አባሶ ባለፉት አመታት ኮቪድን እንዲሁም ግጭቶችን ለማቆም በሁሉም አካላት የተደረገው አይነት የንቅናቄ ስራ የትራፊክ አደጋ ላይም መሰራት አለበት ብለዋል፡፡
አሁን ላይ በሀገሪቷ በተለያዩ አካባቢዎች እየደረሰ ያለው የትራፊክ አደጋ በሽርፍራፊ ሰኮንዶች ከ20 እስከ 60 የሚሆኑ ዜጎችን እየነጠቀ ይገኛል ያሉት ዋና ስራ አስፈጻሚው አደጋውን ለመቀነስ የርብርብ ስራ አስፈላጊ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
የትራፊክ አደጋን መቀነስ ከቻሉ ሀገራት ተሞክሮ በመውሰድ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራና ቀጣይነት ያለው የርብርብ ስራ እንደሚያስፈልግ አቶ ጀማል አንስተዋል፡፡
በቫይታል ስትራቴጂ የመንገድ ደህንነት የኢትዮጵያ ዳሬክተርና ተጠሪ ኢንጂነር ዳንኤል ሞላ ኢትዮጵያ ቀድማ የመንገድ ደህንነትን የሚያስተባብር ተቋም መመስረቷ መልካም ቢሆንም አደጋዎችን ለመቀነስ የሁሉም ባለድርሻ አካላትን ርብርብ ያስፈልጋል ብለዋል።
ለአራት ሳምንት የሚቆይ በፍጥነት ማሽከርከር ላይ ያተኮረ ሀገር አቀፍ የመገናኛ ብዙሃን ንቅናቄ በዛሬው እለት ተጀምራል።
ምላሽ ይስጡ