የቱርኩ ፕሬዝዳንት ሬሲፕ ጣይብ ኤርዶጋን በታህሳስ ወር የቀድሞ የሶሪያ ፕሬዝዳንት ባሻር አል አሳድ ከስልጣን ከተወገዱ በኋላ፣ 200ሺሕ የሶሪያ ስደተኞች ከቱርክ ወደ ሶሪያ መመለሳቸውን አስታውቀዋል።
ኤርዶጋን በቱርክ የፍልሰት አስተዳደር ስብሰባ ላይ እንደተናገሩት በተመሳሳይ ወቅት ከተለያዩ ሀገራት ወደ አገራቸው የተመለሱት ሶሪያውያን አጠቃላይ ቁጥር 931ሺሕ 450 ደርሷል ብለዋል።
በአሁኑ ጊዜ በቱርክ 4 ሚሊዮን ስደተኞች እንዳሉ የገለጹት ፕሬዚደንቱ፣ 2 ነጥብ 8 ሚሊዮን የሚሆኑት ሶርያውያን መሆናቸውን እና በጊዜያዊ ጥበቃ ስር እንደሚገኙ ገልጸዋል። “ይህ ቁጥር ቀስ በቀስ ከቀን ወደ ቀን እየቀነሰ መሆኑን አስታውቀዋል።”
በሶሪያ የተለያዩ ተግዳሮቶች፣ መሰናክሎች እና የጥፋት ድርጊቶች ቢኖሩም ቀስ በቀስ እያገገመች ትገኛለች ሲሉም አክለዋል።
እ.ኤ.አ. በ2011 የእርስ በርስ ጦርነት መቀስቀሱን ተከትሎ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሶሪያውያን አገራቸውን ለቀው መሰደዳቸውን ዘገባው አስታውሷል።
ቱርክ ከሶሪያ ጋር ረጅም ድንበር የምትጋራ ትልቅ መሸሸጊያ አገር እንደሆነች ያስታወቀው ዘገባው፣ ከ3.6 ሚሊዮን በላይ ሶርያውያንን በችግር ጊዜያቸው ወቅት እንዳስተናገደቻቸው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት መረጃን ጠቅሶ ገልጿል።
ዘገባው የአናዶሉ ነው!!!
ምላሽ ይስጡ