የሰሜን ተራሮች ብሄራዊ ፓርክን ባለፉት ዘጠኝ ወራት የጎበኙ የውጭ አገር ቱሪስቶች ቁጥር ከቀደመው በእጥፍ መጨመሩን የፓርኩ ጽህፈት ቤት አስታውቋል፡፡
ብሄራዊ ፓርኩንና በውስጡ የሚገኙ ብርቅየ እንስሳትን የአካባቢውን ማህበረሰብ በማሳተፍ የመጠበቅ ተግባር እየተከናወነ እንደሚገኝ የተመላከተ ሲሆን፤ በዚህም ባለፉት ዘጠኝ ወራት ፓርኩን የጎበኙ የውጭ አገር ቱሪስቶች ቁጥር እንዲጨምር ማድረጉንና የጎብኚዎቹ ቁጥር ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወራት ጋር ሲነጻጸር በእጥፍ ማደጉ ተመላክቷል፡፡
ባለፉት ዘጠኝ ወራት ፓርኩን ከተለያዩ የዓለም አገራት የመጡ 2 ሺህ 723 ቱሪስቶች እንደጎበኙት የተገለጸ ሲሆን፤ በፓርኩ አዋሳኝ ወረዳዎች በኢኮ ቱሪዝም የተደራጁ ማህበራትም ለቱሪስቶች የመጓጓዣ በቅሎ በማከራየት፣ ጓዝ በመጫን፣ መንገድ በመምራትና ምግብ በማብሰል 3 ሚሊዮን ብር የሚጠጋ ገቢ በማግኘት ተጠቃሚ መሆናቸው መገለጹን ኢዜአ ዘግቧል፡፡
ምላሽ ይስጡ