የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት በተያዘው በጀት ዓመት በ9 ወራት ውስጥ 1 ሺህ 451 አምራች ኢንተርፕራይዞች ትስስር በመፍጠር 2 ሺህ 231 አነስተኛና መካከለኛ አምራች ኢንተርፕራይዞች ገቢ ምርቶችን በመተካትና ለሀገር ውስጥ ገበያ በማቅረብ 1 ነጥብ 6 ቢሊየን ዶላር የውጭ ምንዛሬ ማዳን መቻሉን የገለፁት የአንተርፕራይዙ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ አብዱልፈታ የሱፍ ናቸው ።
2 ሺህ 752 አዳዲስ አነስተኛና መካከለኛ አምራች ኢንተርፕራይዞችን ማቋቋም መቻሉንና ነባሮችን የማጠናከርና 151ሺ ለሚሆኑ ዜጎች የስራ ዕድል መፈጠሩን አሰረድተዋል፡፡
ከአነስተኛ ወደ መካከለኛ 979 እንዲሁም ከመካከለኛ ወደ ከፍተኛ 33 ኢንተርፕራይዞች መሸጋገራቸውንና በ9 ወራት የታቀደውንም ማሳካት መቻሉን ገልጸዋል፡፡
በዚህም ከውጪ በተገኘ ድጋፍ የምርቶችን ጥራት በመጨመር ኢንዱስትሪዎችን አለም አቀፍ ተወዳዳሪ በማድረግ ብሎም የገበያ እድልን ከሃገር ውስጥ ባለፈ በሌሎች የአለም ሀገራት በማስፋፋት 10 ቢሊየን ብር የገበያ ትስስር መገኘቱን ገልፀዋል፡፡
ዜጎች ካላቸው ገቢ ተጨማሪ እንዲያገኙ ለማድረግ በመሰራቱ ውጤታማ የ 9 ወር አፈፃፀም እንደነበርና፣ ተቋሙ ከክልል፣ ከዘርፉ ባለድርሻና አጋር አካላት ጋር በመቀናጀት እየሰራ ያለውን ስራ አጠናክሮ እንደሚቀጥል አመላክተዋል፡፡
ምላሽ ይስጡ