የአሜሪካ ቀረጥ በተለይም ዶናልድ ትራምፕ ከተመረጡ በኋላ ያሉት ዓለም አቀፍ የንግድ ግንኙነቶች እንዲሁም ዓለም አቀፋዊው የንግድ ጦርነት ለተለያዩ ሃገራት ስጋት እና እድል ይዞ እንደሚመጣ ሲጠቀስ ቆይቷል፡፡
በንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር የህዝብ ግንኙነት እና የኮሙኒኬሽን ሥራ አስፈጻሚ አቶ ወንድሙ ፍላቴ እንደገለጹት፣ የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ዘርፍ የአንድ አገር አጠቃላይ እድገት ላይ ትልቅ ሚና ያለዉ እንደመሆኑ ለዘርፉ የነዳጅ ፍላጎት እና አቅርቦት ወሳኝነት ጥያቄ ዉስጥ የሚገባ አለመሆኑን ይጠቅሳሉ፡፡
በዚህም በአሜሪካ የሚጣሉ ቀረጦች እንደ ኦፔክ(The Organization of the Petroleum Exporting Countries (OPEC)) ያሉ የነዳጅ ምርት አምራች አገራት ላይ የሚፈጥረዉ ጫና ከፍተኛ በመሆኑ ወደ አሜሪካ ገበያ የሚያሰገቡትን ምርት ቀንሰዉ ወደ ሌሎች ሃገራት ለመላክ እንደሚያስገድዳቸዉ እና ኢትዮጵያ በዚህ ተጠቃሚ ልትሆን እንደምትችል አስረድተዋል፡፡
ምንም እንኳን ዓለም አቀፍ የነዳጅ ዋጋዎች የሚወሰኑት በአለም አቀፍ ገበያ መሆኑ ቢታወቅም ሚኒስቴሩ የዋጋ ቅናሽ ለማድረግ ድርድር ሊያደርግ እንደሚችል ጠቁመዋል፡፡
በተጨማሪሙ አቶ ወንድሙ መንግስት የነዳጅ ዋጋ መጨመር የሚያስከትለውን ስጋት ለመቀነስ በአሁኑ ወቅት አረንጓዴ ኢኮኖሚን በማሳደግ ላይ ያተኮረ ፖሊሲን እየተገበረ በመሆኑ ብሎም የኢትዮጵያን የተፈጥሮ ሃብት በመጠቀም የሚንቀሳቀሱ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች ጥቅም ላይ እንዲዉሉ እየተደረገ በመሆኑ ፤በነዳጅ ላይ የተመሰረተ ትራንስፖርትን ቀስ በቀስ በመቀነስ ለነዳጅ የሚወጣዉን ከፍተኛ የዉጭ ምንዛሬ ለማስቀረት እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
የአሜሪካ የንግድ ፖሊሲ ለኢትዮጵያ ፈተና ሊሆን ቢችልም መንግስት የአረንጓዴ ኢኮኖሚ ልማትን በማስፋፋት እና በአለም አቀፍ ገበያ ላይ ተመጣጣኝ ዋጋ ለማግኘት በመደራደር እነዚህን ተግዳሮቶች ወደ ዕድል መቀየር እንደሚችል የሚኒስቴር መስራ ቤቱ የኮሙኒኬሽን ሥራ አስፈጻሚ አቶ ወንድሙ ፍላቴ አመላክተዋል ።
ምላሽ ይስጡ