ታሪካዊቷን የጎንደር ከተማ የልማት ስራዎችን ለማከናወን የሚያስችል የገቢ ማሰባሰቢያ ፕሮግራም ሚያዚያ 20 ቀን 2017 ዓ.ም ሊካሔድ መሆኑ የጎንደር ከተማ አሥተዳደር ገልጿል።
የጎንደር ከተማ አሥተዳደር “ኑ ጎንደርን እንሞሽር” በሚል መሪ ሐሳብ ለሁለተኛው ዙር የኮሪደር ልማት ሥራ በሀገር ውስጥ እንዲሁም በውጭ የሚገኙ ዜጎች የጎንደርን ቀደምት ከፍታ ለመመለስ በሚሰራው የልማት ስራ የበኩላቸውን አስተዋጽኦ እንዲያበረክቱ የከተማ አስተዳደሩ የገቢ ማሰባሰቢያ ጥሪ አቅርቧል።
ከልማት ስራዎቹ መካከል የኮሪደር ልማት ስራ በዋናነት የሚጠቀስ ሲሆን በሁለተኛ ዙር ለሚከናወነው የኮሪደር ልማት ስራ 1.7 ቢሊየን ብር እንደሚያስፈልግም ተጠቅሷል ።
ዓለም አቀፍ የገቢ ማሰባሰቢያ መርሐ-ግብሩ ሚያዝያ 20 ቀን 2017 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተማ እንደሚካሄድ ተገልጿል።
ምላሽ ይስጡ